am_tn/dan/05/25.md

1.5 KiB

ይህም ፅሕፈት ተፅፏል

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እጁ የፃፈው መልዕክት ይሄ ነው፡፡”

ማኔ፤ቴቄል፤ፋሬስ

እነዚህ በአረማይክ ቋንቋ ግድግዳው ላይ የተፃፉ ቃላት ናቸው፡፡

“ማኔ”…አግዚአብሔር መንግሥትህን ቆጠረው

“ማኔ”ማለት እግዚአብሔር ቆጠረው ማለት ነው፡፡

“ቴቄል” ተመዘንህ

“ቴቄል”ማለት በሚዛን ተመዘንህ ማለት ነው፡፡

“ፋሬስ” መንግሥትህ

“ፋሬስ”ማለት መንግሥትህ ማለት ነው፡፡

በሚዛን ተመዘንክ ቀለህም ተገኘህ

ንጉሱ ግዛቱን የመግዛቱን ጉዳይ በተመለከተ ጠቃሚ መሆን አለመሆኑን ለመናገር በሚዛን እንደሚመዘን ዓይነት ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡ ይሄ ማለት ንጉሱ የመግዛት ብቃት የለውም ማለት ነው፡፡ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር የመግዛት ብቃትህን መዝኖ የመግዛት ብቃት እነደሌለህ ደርሶበታል፡፡”

መንግሥትህ ተከፈለ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እግዚአብሔር መንግሥትህ ከፍሎ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎች ሰጥቷቸዋል፡፡”