am_tn/dan/05/20.md

1.3 KiB

ልቡ ታበየ

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ራሱ ንጉሱን ነው፡፡“ንጉሱ ግትር ሰው ነበር”

መንፈሱ በጠነከረ

እዚህ ላይ“መንፈስ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ራሱ ንጉሱን ነው፡፡ግትር መሆኑ የሚገለፀው ልክ ጠንካራ እንደሆነ በሚመስል መልኩ ነው፡፡

በሚያውክ ሁኔታ

ሥርዓት አልባና ከልክ ባለፈ መልኩ በራስ መተማመን

ከመንግሥቱ ዙፋን ተዋረደ

እዚህ ላይ“ዙፋን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ለመግዛት የሚያበቃውን ኃይል ነው፡፡ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች መንግሥቱን ወሰዱበት”

ከሰው ልጆች ተለየ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች ከአጠገባቸው እንዲሄድ አስገደዱት”

ልቡም እንደ አውሬ ልብ ሆነ

“ልብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አስተሳሰቡን ነው፡፡ “ልክ እንደ እንስሳ ማሰብ”

ጠል

ማለዳ በሚሆንበት ወቅት በመሬት ላይ የሚታይ አርጥበታማ ነገር፡፡

የሚወድደውን ሁሉ

“የሚመርጠውን ሁሉ”