am_tn/dan/05/17.md

1.9 KiB

ሥጦታህ ለአንተ ይሁን

“ሥጦታህን አልፈልገውም”

ወገኖች፤አህዛብና በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩሁሉ

ይሄ ሐረግ“ሁሉ”የሚለውን ቃል የሚጠቀመው ሠፊ ቁጥር ያለውን ሕዝብ አጠቃልሎ ለመግለፅ ነው፡፡“ከተለያዩ ወገኖች የሆኑና የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎች”

ወገኖች፤አህዛብና በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ

እዚህ ላይ “ወገኖች” እና “ቋንቋዎች”የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ከተለያዩ ወገኖች የሆኑና የተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ሕዝቦችን ነው፡፡ትንቢተ ዳንኤል 3፡4ን3 እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡ “ከተለያዩ ወገኖች የሆኑ የተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ሕዝቦች”

ይንቀጠቀጡና ይፈሩ ነበር

በመሠረቱ እነዚህ ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ፍርሃቱ ከፍተኛ ስለመሆኑ አፅንዖት ይሰጣሉ፡፡“በጣም ፈርተውት ነበር”

የፈቀደውን ይገድል

ይሄ ሐረግ ራሱ ናቡከደነፆር ሰዎቹን ገደላቸው ማለቱ ሣይሆን ያዘዛቸው ሰዎች ናቸው ተግባራዊ ያደረጉት ለማለት ነው፡፡“ናቡከደነፆር ሊገድላቸው የፈለጋቸውን ሰዎች ወታደሮቹን በማዘዝ እንዲገደሉ አደረጋቸው፡፡”

የፈቀደውን በሕይወት ያኖር

“ከፍ ለማድረግ የፈለገውን ሰው ከፍ ያደርግ ነበር”

የፈቀደውን..የፈለገውን

እነዚህ ቃላት ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡

የፈቀደውንም ያዋርድ ነበር

“ለማዋረድ የፈለገውን ያዋርድ ነበር”