am_tn/dan/04/36.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡ከቁጥር 34-37 ድረስ ባለው ክፍል ውስጥ ናቡከደነፆር ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ምላሽ በአንደኛ መደብነት ይገልፀዋል፡፡

ጤንነቴ ተመለሰልኝ

እዚህ ላይ ጤንነቱን በተመለከተ የሚገለፀው ልክ ወደ ሥልጣኑ ለመመለስ እንደሚችል ተደርጎ ነው፡፡“ዳግም ጤነኛ ሆንኩ”

ግርማዬና ውበቴ ተመለሰልኝ

እዚህ ላይ ግርማውና ውበቱ የሚገለፁት በራሳቸው ጉልበት የመምጣት ኃይል እንዳላቸው ተደርጎ ነው፡፡“ግርማዬንና ውበቴን በድጋሚ አገኘሁት”

ግርማና ውበት

በመሠረቱ እነዚህ ቃላት ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን የክብሩን ታላቅነት በሚመለከት አፅንዖት ይሰጣሉ፡፡

መኳንንቶቼ ፈለጉኝ

“መነኳንንቶቼ እገዛ እንዳደርግላቸው እንደገና ጠየቁኝ”

ፀናሁ ….ብዙ ክብርም ተጨመረልኝ

እዚህ ላይ “ዙፋን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ፍፁም ገዢ መሆኑን ነው፡፡“በመንግሥቴ ውስጥ እንደገና መግዛት ጀመርኩ፤ከሚገባው በላይ የሆነ ክብር ተጨመረልኝ”

ማመስገን፤ታላቅ ማድረግ፤ማክበር

በመሠረቱ እነዚህ ሶስቱ ቃላት ተመሳሳይ ሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን እግዚአብሔርን ምን ያህል እንዳመሰገነ አፅንዖት ይሰጣል፡፡

በትዕቢት የሚሄዱትን

ይሄ “የሚሄዱ”የሚለው ቃል የሚኮራን ሰው የሚያመለክት ነው፡፡“የሚኮሩ ሰዎች”