am_tn/dan/04/35.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቁጥር 34 እስከ 37 ባሉት ክፍሎች ውስጥ ናቡከደነፆር ለእግዚአብሔር የሰጠውን ምላሽ ለመግለፅ በሶስተኛ መደብነት ይናገራል፡፡

በምድር የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቆጠራሉ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በምድር ነዋሪ የሆኑትን ሁሉ እንደ ምናምን ነው የሚቆጥራቸው”

በምድር የሚኖሩ ሁሉ

“በምድር ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ”

የሰማይ ሠራዊት

“በሰማይ ውስጥ የሚገኙ የመላዕክት ሠራዊቶች”

እንደ ፈቃዱ

“ዓላማው ግቡን እስከመታ ድረስ”ወይም “ማከናወን የሚፈልገውን ሁሉ”

የሚከለክለው የለም

ተጨማሪ ዝርዝር ነገር መጨመሩ ያስፈልግ ይሆናል፡፡“አንድ ነገር ለማድረግ ከወሰነ ማንም ሊያቆመው አይችልም”

ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም

ይሄ ቀጥተኛ ባልሆነ አባባል ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንድ ነገርን ሲያከናውን ጥያቄ ለመጠየቅ የሚደፍር ሰው አይኖርም”