am_tn/dan/04/31.md

978 B

አጠቃላይ መረጃ

ከቁጥር19-33 ያለው ክፍል የናቡከደነፆርን ቅጣት ለመግለፅ ሶስተኛ መደብን ይጠቀማል፡፡

ቃሉም ገና በንጉሡ አፍ ሳለ

የዘይቤያዊ አነጋገሩ ፍቺ እየተናገረ እያለ መሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡“ንጉሡ በመናገር ላይ ሳለ”

ድምፅ ከሰማይ ወደቀ

“ድምፅን ከሰማይ አዳመጠ”

ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ …ከአንተ ተወሰደ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ንጉሥ ናቡከደነፆር ሆይ ይሄ መንግስት ከአንተ እንደተወሰደ አዋጅ ወጥቷል፡፡”

ከሰዎች ተለይተህ ትሰደዳለህ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ሰዎች ከአጠገባቸው እንድትሄድላቸው ያስገድዱሃል”

ለሚወድደው

“ለሚፈልገው ሰው”