am_tn/dan/04/26.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቁጥር19-33 ያለው ክፍል የናቡከደነፆርን ቅጣት ለመግለፅ ሶስተኛ መደብን ይጠቀማል፡፡

ሥልጣን ከሰማያት ነው

እዚህ ላይ“ሰማይ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሰማይ ውስጥ የሚኖረውን ነው፡፡“በሰማይ ውስጥ የሚኖረው እግዚአብሔር የሁሉም ገዢ ነው፡፡”

ምክሬ ደስ ያሰኝህ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እባክህን ምክሬን ተቀበለኝ”

ከበደል ተመለስ

እዚህ ላይ ከበደል ተመለስ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከበደል ዘወር ማለትን ነው፡፡“በደልን ተቃወመው”

የተጨቆኑት

ይሄ መለስተኛ ቅፅል የሚያመለክተው የተጨቆኑ ሰዎችን ነው፡፡“የተበደሉ ሰዎች”

ባለፀግነትህ ይቆይልሃል

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅም ይችላል፡፡“እግዚአብሔር ባለፀግነትህን ሊያራዝመው ይችል ይሆናል”