am_tn/dan/04/19.md

1.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ከቁጥር 19 እስከ 33 ድረስ የሚገኙት ክፍሎች የናቡከደነፆርን ቅጣት በሚመለከት ሶስተኛ መደብን በመጠቀም ነው የሚናገሩት፡፡

ብልጣሶር የሚል ስያሜም ያለው

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“እኔ ብልጣሶር የሚል ስም የሰጠሁት”

ለጥቂት ጊዜ አሰበ፤ልቡም ታወከ

ዳንኤል የፈራበት ምክኒያት የራዕዩን ትርጉም ስለተረዳ ነው፡፡ይሄ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡ “የሕልሙ ትርጉም ስላሰጋው ለጥቂት ጊዜ ምንም ነገር አልተናገረም ነበር፡፡”

ሕልሙ ለሚጠሉህ፤ፍቺውም ለጠላቶችህ ይሁን

ምንም እንኳን ሕልሙ ንጉሡን እንደሚመለከት ያወቀ ቢሆንም የዳንኤል ምኞት ግን ሕልሙ ከናቡከደነፆር ጋር የተያያዘ እንዳይሆን ነበር፡፡