am_tn/dan/03/15.md

1.8 KiB

እንቢልታ…በገና….ዋሽንት

እነዚህ የሙዚቃ መሣሪያዎች ናቸው፡፡እነዚህን በትንቢተ ዳንኤል 3፤5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት አስተውሉ፡፡

መደፋት

እዚህ ላይ “መደፋት”ማለት“በፍጥነት መጋደም” ነው፡፡

መደፋት

ፊታችሁን ወደ ታች አድርጋችሁ መሬት ላይ ለአምልኮ ተደፉ፡፡

መልካም ይሆናል

“ችግር የሚባል ነገር አይኖርም”ወይም “በነፃነት ትሄዳላችሁ” በነፃ ትለቃቃላችሁ፡፡

እኔ የሠራሁት የወርቁ ምሥል

ናቡከደነፆር ይህንን ሥራ ያከናወነው ራሱ ሣይሆን የራሱን ሰዎች ሥራውን እንዲከናውኑት በማዘዝ ነበር፡፡“የእኔ ሰዎች ያቆሙት የወርቅ ምሥል”

በፍጥነት በሚነድድ እሣት ውስጥ ትጣላላችሁ

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“ወታደሮቼ ከመቅፅበት ወደሚነድድ እሣት ውስጥ ይጥሏችኋል፡፡”

የሚነድድ እሣት

ይሄ በእሣት የተሞላ ሠፊ ቦታን የሚያመለክት ነው፡፡ይህንን በትንቢተ ዳንኤል 3፤6 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት አስተውሉ፡፡

አምላክ ማን ነው?…የእኔ እጆች

ንጉሡ መልስ እንዲሰጠው አይጠብቅም፡፡ሶስቱን ሰዎች እያስፈራራቸው ነው፡፡“ከእኔ እጅ የሚያድናችሁ አምላክ የለም” እዚህ ላይ“እጅ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የመቅጣት ብቃት ያለው ሥልጣንን ነው፡፡“ከእኔ ቅጣት”