am_tn/dan/03/13.md

1.7 KiB

በብስጭትና በቁጣ ተሞላ

የናቡከደነፆር ብስጭትና ቁጣ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሣ ልክእ በሆነ ነገር እንደሞሉት ዓይነት ተደርጎ ተገልፆአል፡፡“ብስጭት” እና“ቁጣ” የሚሉት ቃላት ተመሣሣይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን እነዚህ ቃላት ጥቅም ላይ የዋሉት ንጉሡ ምን ያህል እንደታወከ አፅንዖት ለመሥጠት ነው፡፡“ከገደብ ያለፈ ቁጣ”

ሲድራቅ…ሚሣቅ….. አብደናጎም

እነዚህ የዳንኤል ጓደኞች የሆኑ ሰዎች የባቢሎናውያን ስሞች ናቸው፡፡እነዚህን በትንቢተ ዳንኤል 1፤7 ላይ እንደተረጎማችሁት አስተውሉ፡፡

አሁንም ሃሣባችሁን አልለወጣችሁም?

እዚህ ላይ “ሃሣብ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የመወሰንን ጉዳይ ነው፡፡“ሃሣባችሁን አልለወጣችሁም?”ማለት በውሳኔ መሸፅናትን የሚያመለክት ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡“በውሳኔያችሁ እንደፀናችሁ ናችሁ?”

ስገዱ

እነዚህ ሶስት ሰዎች ለምሥሉ አምልኮ ለመስጠት ሲሉ ይሄንን ተግባር ለመፈፀም ፈቃደኞች አይደሉም፡፡“ ፊትን ወደ ታች አድርጎ ለአምልኮ መሬት ላይ መደፋት”

እኔ ላቆምኩት የወርቁ ምሥል

ናቡከደነፆር ይህንን ሥራ ያከናወነው ራሱ ሣይሆን የራሱን ሰዎች ሥራውን እንዲከናውኑለት በማዘዝ ነበር፡፡“የእኔ ሰዎች ያቆሙት የወርቅ ምሥል”