am_tn/dan/03/03.md

1.7 KiB

የአውራጃ ገዢዎች፤የክልል አዛዦች…አውራጃ ገዢዎች

በትንቢተ ዳንኤል 3፡1 ላይ እንዴት አድርጋችሁ እንደተረጎማችሁት አስተውሉ፡፡

ናቡከደነፆር ያቆመው ምሥል

ናቡከደነፆር ይህንን ሥራ ያከናወነው ራሱ ሣይሆን የራሱን ሰዎች ሥራውን እንዲከናውኑት በማዘዝ ነበር፡፡“የናቡከደነፆር ሰዎች ያቆሙት ምሥል”

አዋጅ ነጋሪ

ይሄ ሰው ይህንን ሥራ እንዲሰራ ኃላፊነት የተሰጠው ለንጉሡ አዋጅ ነጋሪ ነው፡፡

ታዝዛችኋል

ይሄ በገቢር መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡“በንጉሡ ታዝዛችኋል፡፡”

ወገኖች፤አህዛብና በልዩ ልዩ ቋንቋዎች የምትናገሩ

እዚህ ላይ “ወገኖች”እና “ቋንቋዎች”የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ከተለያዩ ወገኖች የመጡትንና የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሰዎችን ነው፡፡“የተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩና ከተለያዩ ነገዶች የመጡ ሰዎች”

እምቢልታ

እነዚህ የሙዚቃ መሣሪያዎች ከበገና ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው፡፡ሶስት ማዕዘን የሚመስል ቅርፅ ያላቸው ሆነው አራት ክሮች ያሏቸው ናቸው፡፡

ስገዱ

እዚህ ላይ “ስገዱ” ማለት “መሬት ላይ ተኙ”ማለት ነው፡፡

እንድትደፉ

“በአምልኮ ውስጥ በመሆን ፊታችሁን ወደ ታች አድርጋችሁ መሬት ላይ ተኙ”