am_tn/dan/03/01.md

1.0 KiB

ናቡከደነፆር የወርቅ ምሥል አሰራና አቆመው

ናቡከደነፆር ይህንን ሥራ ያከናወነው ራሱ ሣይሆን የራሱ ሰዎች ሥራውን እንዲያከናውኑ በማዘዝ ነበር፡፡“ናቡከደነፆር የወርቅ ምሥሉን እንዲሰሩ የራሱን ሰዎች አዘዘ….እንዲቆም አደረጉት”

ቁመቱ ስድሳ ክንድ፤ወርዱም ስድስት ክንድ

አንድ ክንድ 46 ሴንቲ ሜትር ነው፡፡“በግምት 27 ሜትር ቁመት ያለውና ወደ 3 ሜትር የሚጠጋ ስፋት ያለው ነው“

የዱራ ሜዳ

ይሄ ሥፍራ የሚገኘው በባቢሎን የወሰን ክልል ውስጥ ነው፡፡

መኳንንት… ሹማምንቶች…አዛዦች

እነዚህ በግዛቱ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የተመደቡ ሰዎች ናቸው፡፡

በጅሮንዶች

እኒዚህ ባለሥልጣናት ኃላፊነታቸው ከገንዘብ ጋር የተያያዘ ነው፡፡