am_tn/dan/02/36.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ዳንኤል ለንጉሡ መናገሩን ይቀጥላል

አሁንም በንጉሡ ፊት እንናገራለን

እዚህ ላይ “እኛ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ዳንኤልን ነው፡፡ ምናልባትም የብዙ ቁጥርን የተጠቀመው ለራሱ ላለማድላት ሲልና እግዚአብሔር የገለፀለትን የሕልሙን ትርጉም ስላሳወቀ ከትህትና የተነሣ ያደረገውም ሊሆን ይችላል፡፡

የነገሥታት ንጉሥ

“እጅግ ተፈላጊ የሆነ ንጉሥ” ወይም “በሌሎች ንጉሶች ላይ ገዢ የሆነ ንጉሥ”

ኃይሉ፤ብርታቱ

እነዚህ ቃላት በመሠረቱ ተመሳሳይ ሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡

ሥፍራውን ሁሉ በእጅህ አሣልፎ ሰጥቷል

እዚህ ላይ“እጅ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው መግዛትን ነው፡፡“ሥፍራውን በቁጥጥራችሁ ሥር እንድታደርጉ አድርጓችኋል፡፡”

የሰው ልጆች የሚቀመጡበት ሥፍራ

ሥፍራው የሚያመለክተው በዚያ ሥፍራ ነዋሪ የሆኑ ሰዎችን ነው፡፡“የምድሪቱ ሰዎች”

እንስሳትን በእጅህ አሣልፎ ሰጥቷል

እዚህ ላይ“እጅ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው መግዛትን ነው፡፡“በሜዳ ላይ በሚገኙ እንሥሳትና የሰማይ ወፎች ላይ እንድትገዟቸው አሣልፎ ሰጥቷችኋል፡፡”

የሰማይ አዕዋፍ

እዚህ ላይ“የሰማይ”የሚለው ሃሣብ “ሰማያት” የሚለውን ቃል ለመወከል የዋለ ነው፡፡

አንተ የወርቁ ራስ ነህ

በንጉሡ ሕልም ውስጥ የምስሉ ራስ የሚወክለው ንጉሡን ነው፡፡“የወርቅ ምሥሉ የሚወክለው አንተን ነው” ወይም “የወርቁ ራስ የአንተና የሥልጣንህ ምልክት ነው”