am_tn/dan/01/08.md

1.6 KiB

ዳንኤል በአዕምሮው አሰበ

እዚህ ላይ “አዕምሮ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ራሱን ዳንኤልን ነው፡፡

ራሱን ማርከስ

አንድን ነገር “እንዲረክስ ማድረግ” ማለት ንፁህ እንዳይሆን ማድረግ ማለት ነው፡፡ በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት አንዳንድ የባቢሎናውያን ምግቦችና መጠጦች ከአምልኮ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ሊያረክሱት ይችላሉ፡፡ይሄ የበለጠ ሊብራራ ይችላል፡፡ “ከእግዚአብሔር ሕግ አንፃር የሚታይ ከሆነ ራሱን ለርኩሰት አሣልፎ ይሰጣል ማለት ነው”

ቅንጡ የሆኑ ነገሮች

ይሄ ልዩ የሆኑ፤በተራው ሕዝብ ዘንድ ያልተለመዱና መልካም ምግቦችን የሚመለከት ነው፡፡

ከአንተ ዕድሜ እኩያ ከሆኑ ብላቴኖች ጋር ስትታይ ለምን የተጎዳህ ሆነህ ይመልከትህ?

ኃላፊው ሰው ይህንን ጥያቄ የጠየቀበት ምክኒያት ያለው ነገር ሊከሰት ይችላል ብሎ በማሰቡ ነው፡፡እንደ መግለጫም ሊሆን ይችላል፡፡“ በዕድሜ የአንተ እኩያ ከሆኑ ከሌሎች ወጣት ልጆች በባሰ ሁኔታ ተጎሳቁለህ ሊያይህ አይሻም”

ንጉሡ አንገቴን ሊቆርጠው ይችላል

ይሄ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡“ንጉሡ ራሴን ሊቆርጠው ይችላል” ወይም “ንጉሡ ሊገድለኝ ይችላል”