am_tn/col/02/13.md

2.2 KiB

ቆላስያስ 2፡ 13-15

ሙታን በሆናች ጊዜ "የቆላስያስ አማኞች በመንፈሳዊ ሞት ውስጥ በነበሩበት ጊዜ" በመተላለፋችሁ ሙታን ነበራችሁ እንዲሁም በሥጋችሁም ያልተገረዛችሁ ነበራችሁ በሁለት ነገሮቸ ሙታን ነበሩ: 1) በመንፈሳዊ ሕይወት ሙታን፣ ክርስቶስ የሚበድል ኃጢአት የሞላበትን ሕይወት ትኖሩ ነበር እና 2) እንደ ሙሴ ሕግ የተገረዛችሁ አልነበራችሁም፡፡ እርሱ እናንተን እንዲህ አደረጋችሁ "ኢየሱስ እናንተን የቆላስያስ አማኞችን እንዲህ እንዲትሆኑ አደረገ" መተላለፋችንን ሁሉ ይቅር አለን "ኢየሱስ ክርስቶስ አይዳዊያንን እና አሕዛብን ሁለቱን መተላለፋችንን ሁሉ ይቅር አለልን፡፡" እናንተ ሙታን ነበራችሁ . . . ሕያዋን እንዲትሆኑ አደረገ ይህ ምሳሌዊ ንግግር ልክ የሞተ ሰው ወደ ሕይወት በአካል እንደሚመጣ ሁሉ እኛም እንዴት ኃጢአተኛ ከሆነ ሕይወት ወደ አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት እንደመጣን ያሳያል፡፡(ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/figs-metaphor) በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤

ይህ ምሳሌያዊ ንግግር እግዚአብሔር የእኛን ኃጢአት (እዳ) እና የእግዚአብሔርን ሕግ መተላለፋችን መሰረዙን በወረቀት ላይ የተጸፉ ዝርዝሮችን ከመሰረዝ ጋር እያነጻጸረ ያቀርባል፡፡ (ተመልከት: rc://*/ta/man/translate/figs-metaphor) ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው። በሮማዊያን ዘመን የሮም ወታደሮች ከጦርነት ሲመለሱ “የድል ጉዞ” ማድረግ የተለመደ ነገር ነው፡፡ በዚህ ወቅት በምርኮ የያዝዋቸውን ምርኮኞች እና የነጠቁትን ሀበት ያሳያሉ፡፡