am_tn/col/02/01.md

2.7 KiB

ቆላስያስ 2፡ 1-3

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ጳውሎስ በቆላስያስ እና በሎዶቂያ የሚገኙ አማኞች ክርስቶስ አምላክ እንደሆነ እና በአማኞች ውስጥ እንደሚኖር ተገንዝበው እርሱን በተቀበሉበት መቀበል መኖር እንዳለባቸው ማበረታታቱን ቀጥሏል፡፡ ስለዚህ ይህንን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ "እኔ ጳውሎስ በቆላስያስ የሚትኖሩ አማኞች ይህንን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ" እንዴት ያለ ትልቅ መጋደል እንዳለኝ ልታውቁ እወዳለሁና፤ የእርሱን ንጽሕና ለማሳደግ እና የወንጌል መረዳታቸቸውን ለመጨመር ጳውሎስ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ በሎዶቅያ ላሉት ይህች ከተማ የቆላስያስ ከተማ ቅርብ የሆነች ከተማ ሲትሆን በዚህች ከተማ ውስጥመም ቤተ ክርስቲያን ነበረች፣ ጳውሎስም ለዚህች ከተማ ይጸልይላታል፡፡ ብዙዎች በሥጋ ፊቴን የማየት እድል አላገኙም "ብዙዎቹን በአካል አላገኘኋቸውም" ወይም "ብዙዎችነን ፈጽሞ ፊት ለፊት አግኝቼአቸው አላውቅም" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-synecdoche]]) ልባቸውም "ጳውሎስን በአካል አይተውት የማያውቁት ሁሉም አማኞች ልብ" ወደ አንድነት እንዲሰበሰብ በእውነተኛ ግንኙነት እንድቀራረቡ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "እርስ በእርሳቸው እንዲተባበበሩ" ወይም "እርስ በእርሳቸው እንዲቀራረቡ" ከመረዳት የሚመጣ መተማመን ይህ እነዚህ ነገሮች በማወቅ የሚገኝ መተማመን ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ምስጢር ይህ በእግዚአብሔር ስገለጥ ብቻ የሚታወቅ ነገር ነው፡፡ ይኼውም ክርስቶስ ነው ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር የተገለጠ ምስጢር ነው፡፡ የጥበብ እና እውቀት የተደበቀ መዝገብ ታላቅ የጥበብ እና የእውቀት ሀብት ወይም ባለጠግነት ጥበብ እ እውቀት እነዚህ ቃላት በመሠረታዊ ሀሳባቸው ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ጳውሎስ እነዚህ ቃላት በአንድነት የተጠቀመው ሁሉም መንፈሳዊ መረዳቶች ከክርስቶስ ዘንድ አንደሚመጡ አጽኖት ለመስጠት ነው፡፡ (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-doublet]]) በእርሱ ናቸው “እርሱ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ክርስቶስን ነው፡፡