am_tn/amo/09/13.md

2.3 KiB

እዩ

ፀሐፊው አንድ አስደናቂ የሆነ ነገርን ሊናገር እንደተዘጋጀ ለአንባቢያን ይናገራል፡፡ምናልባት ቋንቋችሁ ይህንን የሚገልፅበት መንገድ ሊኖረው ይችል ይሆናል፡፡

ወራት ይመጣል… አራሹ

ወደፊት የሚመጡ ቀናቶች “ወራት እንደሚመጡ” በሚመስል መልኩ ተገልጿል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ወራት ይመጣል…አራሹ ሰው”ወይም “ወደፊት…አራሹ ሰው”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አራሹ… ዘርን የሚዘራው

እነዚህ እግዚአብሔር በእሥራኤል ውስጥ ባለፀግነትን ዳግም ለማምጣት መፈለጉን የሚያሣዩ ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ይሄ የሚያሣየው እህል እጅግ በፍጥነት ከማደጉ የተነሳ ሰዎች እህሉን ለመሰብስብ የሚያዳግታቸው እንደሆንና ብዙ የወይን ፍሬ ከመኖሩ የተነሳ ሰዎች ወይኑን ገና እየጠመቁ እያሉ ገበሬዎች ሌላ ተጨማሪ የወይን እርሻን የሚያርሱ መሆናቸውን ነው፡፡

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ስለ ራሱ በራሱ ሥም ይናገራል፡፡ይሄንን በአሞፅ 3፤13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡የአሞፅ ትርጉም “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚናገረው ይህንን ነው” ወይም “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ያለው ይሄንን ነው”(የመጀመሪያ፤ሁለተኛና ሦስተኛ የሚለውን ይመልከቱ)

ተራሮችም በተሃውን የወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፤ኮረብቶችም ሁሉ ይቀልጣሉ

እነዚህ ሁለት መሥመሮች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡እጅግ ብዛት ያላቸው የወይን ዘለላዎችና ወይኖች ልክ በተራሮችና በኮረብታዎች ላይ እንደሚፈስሱ ተደርጎ ነው የቀረበው፡፡(ንፅፅርንን እና ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)