am_tn/amo/09/11.md

2.7 KiB

በዚያ ቀን

“በዚያን ዘመን”

የወደቀችውን የዳዊትን ድንኳን አነሣለሁ

የእሥራኤልን ሕዝብ እንደገና ታላቅ ማድረግን በተመለከተ ልክ የዳዊት ምንግሥት ድንኳን እንደሆነና እግዚአብሔር ደግሞ አንስቶ አንደገና እንደሚተክለው ተደርጎ ቀርቧል፡፡የአሞፅ ትርጉም “የዳዊት ድንኳን ልክ እንደወደቀ ድንኳን ቢሆንም እንኳን እርሱ ግን መልሶ ያቆመዋል፡፡”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የተናደውንም ቅጥሯን እጠግናለሁ

“ቅጥሯን አድሳለሁ”

የፈረሰውንም አድሳለሁ፤እንደ ቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ

“የፈሰውን እንደገና አድሼ ከብዙ ዘመን በፊት እንደነበረችው ጠንካራ አድርጌ አቆማታለሁ፡፡”

አዳራሾች

ወድቀው የቀሩ የየአዳራሾቹየተወሰኑ ክፍሎች

የኤዶምያስ ቅሬታ

“የቀረው የኤዶምያስ ግዛት”

ስሜ የተጠራባቸውን አህዛብን ሁሉ

እዚህ ላይ “ስም” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው፡፡“በስሜ የተጠሩት”የሚለው አነጋገር ትርጉሙ በአንድ ወቅት የእግዚአብሔር ንብረት እንደነበሩየሚያሣይ ነው፡፡ ይሄ ማለት ባለፉት ጊዜያት ሕዝቡ ድልን አግኝተው እነዚህን ግዛቶች ተቆጣጥረዋቸው ነበር ማለት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ለእኔ የነበሩ አህዛብ ሁሉ”ወይም “ባለፉት ጊዜያት እሥራኤላውያን ድል እንዲነሷቸው ያደረግኳቸውን አህዛብ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል፤ፈሊጣዊ አነጋገር፤በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ስለ ራሱ በራሱ ሥም ይናገራል፡፡ይሄንን በአሞፅ 3፤13 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡የአሞፅ ትርጉም “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚናገረው ይህንን ነው” ወይም “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ያለው ይሄንን ነው”(የመጀመሪያ፤ሁለተኛና ሦስተኛ የሚለውን ይመልከቱ)