am_tn/amo/09/09.md

1.8 KiB

የእሥራኤል ቤት

እዚህ ላይ “ቤት” የሚለው ቃል የሚያመለክትው ቤተሰብን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የእሥራኤል ሕዝብ”( ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

እህልም በወንፊት አንደሚነፋ የእሥራኤልን ቤት በአህዛብ መካካል እነፋለሁ፡፡ነገር ግን አንዲት ቅንጣት በምድር ላይ አትወድቅም

እዚህ ላይ የሚያሣየው እህል በወንፊት ውስጥ ሲያልፍና ደንጋዮቹ ተንገዋለው ሲቀሩ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም፡- ኃጢአተኛ የሆነውን የእሥራኤልን ሕዝብ እግዚአብሔር ያስወግደዋል የሚል ሃሣብ ነው ያለው፡፡(ተነፃፃሪ የሚለውን ይመልከቱ)

ወንፊት

ብዙ ቀዳዳዎች ያሉት ወለል ሲሆን ትልልቅ ነገሮችን በውስጡ የማያሣልፍ ነው፡፡

የሕዝቤ ኃጢአተኞች ሁሉ በሠይፍ ይወድቃሉ

እዚህ ላይ“ሠይፍ” የሚለው ቃል የሚመለክተው ጠላቶችን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም“ጠላቶች የሕዝቤን ኃጢአተኞች ሁሉ ይገድላሉ”( ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ )

ክፉው ነገር አይደርስብንም፤አያገኘንም

ጥፋትን መተግበር ልክ ጥፋት አንድን ሰው እንደሚውጠውና እንደሚያገኘው ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ጥፋት እኛን ሊያገኘን አይችልም”ወይም “መጥፎ ነገር አይደርስብንም” (ሲ ሜታፎር)