am_tn/amo/09/05.md

3.7 KiB

ሙላዋም እንደ ወንዝ ትነሣለች እንደ ግብፅ ወንዝም ትወርዳለች

እዚህ ላይ“ወንዙ”እና “የግብፅ ወንዝ” የሚሉት ሁለቱም ቃላት የሚያመለክቱት የናይልን ወንዝ ነው፡፡እግዚአብሔር ምድሪቱ እንድትናወጥ የሚያደርግበትን መንገድ ከናይል ወንዝ መነሳትና መስጠም ጋር ያነፃፅረዋል፡፡(ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ (ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ))

ደረጃዎቹን በሰማይ ላይ የሰራ

ይሄ ምናልባት የጥንት ሰዎች ወደ እግዚአብሔርቤተመንግሥት የሚያመራው መንገድ በደረጃዎች ነው ብለው ስለሚያስቡ ይሆናል፡፡ሆኖም አንዳንድ ቅጂዎች “ቤተመንግሥት” እና “ክፍሎች”የሚል ትርጉም ባለውበተለየ የዕብራይስጥ ቃል እንዲነበብ ይፈልጋሉ፡፡እዚህ ላይ “ደረጃዎቹ”የሚለው ቃል የእግዚአብሔር መንግሥት ለሚለው ቃል ተመሳሳይ ሃሣብ ያለው ሊሆን ይችላል፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ጠፈሩንም በምድር ላይ የመሠረተ

እዚህ ላይ“ጠፈር” የሚለው ቃል የመፅሐፍ ቅዱስ ፀሐፊዎች የሚገልፁት በምድር ላይ እንዳለ ጉልላት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ሠማይን በምድር ላይ ይዘረጋል፡፡”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የባህሩንም ውኃ ጠርቶ….. በምድር ፊት ላይ

ይሄ የሚያመለክተው የባህር ውኃ በምድር ላይ እነደ ዝናብ እንዲዘንብ ማድረጉን ነው፡፡በአሞፅ 5፡8 ላይ ይሄንን እንዴት እንደምትተረጉሙት ተመልከቱ፡፡ኤቲ “ውኃውን ወስዶ በምድር ላይ እንዲዘንቡ ያደርጋቸዋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ስሙ ነው

እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ለማከናወን ኃይሉንና ሥልጣኑን ያውጃል፡፡ይሄንን በአሞፅ 2፤111 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡የአሞፅ ትርጉም “አዎ የእሥራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር አወጣሁ፤ፍልሥጤማውያንንም ከከፍቶር ሶርያውንንም ከቂር አወጣሁ፡፡”የአሞፅ ትርጉም(በሙያ ላይ የተደገፈ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ቂር

በአሞፅ 1፤5 ላይ የዚህን ሥፍራ ሥም እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡

የእግዚአብሔር ዓይኖች በኃጢአተኞች መንግሥት ላይ ናቸው

እዚህ ላይ “ዓይኖች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር ስለራሱ በሶስተኛ አካልነቱ ሲናገር ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “እኔ እግዚአብሔር የዚህ መንግሥት ሰዎች እጅግ ኃጢአተኞች እንደሆኑ አይቻለሁ” (ሚቶኖሚ አንደኛ፤ሁለተኛና ሶስተኛ አካልን ይመልከቱ)

ከምድርም ፊት አጠፋታለሁ

“ከምድርም ፊት”የሚለው አነጋገር “ሙሉ በሙሉ” ማለት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም“ይህንን መንግሥት ሙሉ ለሙሉ አጠፋዋለሁ” (ፈሊጣዊ አነጋገርን ተመልከቱ)