am_tn/amo/09/03.md

1.7 KiB

በቀርሜሎስ ራስ ውስጥ ቢሸሸጉ ….በጥልቅ ባህርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ

እግዚእብሔር ወደ ቄርሜሎስ ተራራ ራስ ሊሸሸጉ የሚሮጡትን ወይም ለመደበቅ ወደ ጥልቅ ባህር የሚሄዱትን በሚመለከት የተጋነነ ገፅታን ያቀርባል፡፡እዚህ ላይ “በቀርሜሎስ ራስ”እና “ጥልቅ ባህር”ሥፍራዎችን ሁሉ የሚያመለክቱ ምሕፃረ ቃሎች ናቸው፡፡የአሞፅ ትርጉም “በቄርሜሎስ ራስ ላይ ቢሸሸጉ እንኳን…የማላይ መስሏቸው ወደ ባህር ጥልቅ ለመሄድ ቢሞክሩ እንኳን”(ሆን ብሎ አጋኖ መናገርን፤አጠቃላይነትንና ምሕፃረ ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

እባብ

ያልታወቀ አደገኛ እንስሳ፤በኤደን ገነት የታየው ወይም በተለምዶ የምናውቀው ዓይነት እባብ ያልሆነ፡፡

በጠላቶቻቸውም ተማርከው ቢሄዱ

ይሄ አድራጊ ግሥ መልክ ሊገለፅ ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ጠላቶች ቢማርኳቸውና ወደ ባዕድ አገር ይዘዋቸው ቢሄዱ እንኳን ”(አድራጊ ግሥን ወይም ተካፋይ ያልሆነ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያ ሰይፍን አዝዛለሁ እርሱም ይገድላቸዋል

እዚህ ላይ“ሠይፍ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጠላቶችን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “እዚያ ጠላቶቻቸው እንዲገድሏቸው አደርጋለሁ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)