am_tn/amo/09/01.md

3.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር ለአሞፅ ሌላ ራዕይን ያሣየዋል፡፡

በራሣቸውም ሁሉ ላይ ሰባብራቸው

እግዚአብሔር እነዚህን ትዕዛዛት ለማን እንደሚናገር ግልፅ አይደለም፡፡

መድረኮቹ ይናወጡ ዘንድ ፤ጉልላቶቹን ምታ

ይሄ እግዚአብሔር ስለ ጉልላቶቹና ስለ መቅደሱ መሠረቶች በተገናኘ መልኩ የተናገረው ነገር ነው፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀት የሚለውንና ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መድረኮቹ ይናወጡ ዘንድ

እዚህ ላይ “መድረኮቹ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቤተ መቅደሱን በአጠቃላይ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ቤተ መቅደሱ በሙሉ ይናወጥ ዘንድ”(አጠቃላይ ሃሣቡን በአጭር ንግግር የመግለፅ ዘዴ የሚለውን ይመልከቱ)

በራሳቸውም ላይ ሰባብራቸው

እዚህ ላይ“ራስ”የሚለው ቃል በአጠቃላይ ማንነቱን የሚያመለክት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “መቅደሱ በሰዎች ላይ ወድቆ ይገድላቸው ዘንድ ጉልላቶቹን ምታ”(አጠቃላይ ሃሣቡን በአጭር ንግግር የመግለፅ ዘዴ የሚለውን ይመልከቱ)

የቀሩትን በሰይፍ እገድላለሁ

እዚህ ላይ“ሰይፍ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ተዋጊዎች በሠይፋቸው የሚያጠቁበትን ሁኔታ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የተቀሩትን የሚገድል የጠላት ሠራዊትን እልካለሁ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ሲዖል ቢወርዱ እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ወደ ወደ ሰማይም ቢወጡ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ

እግዚአብሔር ወደ ሲዖል የሚሰደዱበትን ሁኔታ ወይም ሞትን ለማምለጥ ሲሉ ወደ ሰማይ የመሄዳቸውን ጉዳይ የተጋነነ በሚመስል መልኩ አቅርቦታል፡፡እዚህ ላይ “ሲዖል” እና “ሰማይ”እንደ ምሕፃረ ቃል ሆኖ ሥፍራዎችን በሙሉ የሚወክል ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ወደ ሲዖልና ወደ ሰማይ ቢሄዱ እንኳን ከእኔ ሊያመልጡ አይችሉም፡፡” (ሆን ብሎ አጋኖ መናገርን፤አጠቃላይነትንና ምሕፃረ ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች

እዚህ ላይ“እጅ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ኃይል ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ከዚያ አወጣቸዋለሁ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)