am_tn/amo/08/11.md

2.6 KiB

ዘመን ይመጣል

ይሄ ልክ ቀኑ ራሱ “እየተራመደ እንደሚመጣ” ዓይነት ተገልጿል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ቀን ይመጣል” ወይም “ለወደፊቱ” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ስለ ራሱ በራሱ ሥም ይናገራል፡፡ይሄንን በአሞፅ 4፤5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡የአሞፅ ትርጉም “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚናገረው ይህንን ነው” ወይም “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ያለው ይሄንን ነው” (የመጀመሪያው፤ሁለተኛውንና ሦስተኛውን ይመልከቱ)

እነሆ በምድር ላይ ራብን በምሰድድበት ዘመን …የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት እንጂ

ሰዎች ከእግዚአብሔር መልዕክት ለመስማት ፈልገው እግዚአብሔር ለመናገር ፈቃደኛ ስለማይሆንየቃሉ ረሃብ እንደሚመጣባቸው ተደርጎ ነው የተገለፀው፡፡የአሞፅ ትርጉም “በምድሪቱ ውስጥ ከረሃብ ጋር የሚመሳሰል ነገር በማመጣበት ወቅት… ሆኖም የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ቃል

ይሄ በመጀመሪያው ማንነት ሊገለፅ ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ከእኔ የሆነ ቃል፤እግዚአብሔር”ወይም “የእኔ መልዕክቶች” (የመጀመሪያ፤ሁለተኛና ሦስተኛ የሚለውን ይመልከቱ)

ከባህርም እስከ ባህር ድረስ ከሰሜንም እስከ ምሥራቅ ድረስ ይቅበዘበዛሉ

እዚህ ላይ“ከባህር እስከ ባህር”እና “ከሰሜን እስከ ምሥራቅ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእሥራኤልን ምድር ሁሉ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የእግዚአብሔርን ቃል ለማግኘት እዚህና እዚያ እያሉ ይቅበዘበዛሉ፡፡”(ምሕፃረ ቃል የሚለውን ይመልከቱ))

ከባህር እስከ ባህር ድረስ

ይሄ የሚያመለክተው በደቡብ በኩል ሙት ባህርንና በምዕራብ በኩል ደግሞ የሜዲቴሪያን ባህርን ነው፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀት የሚልውን ይመልከቱ)