am_tn/amo/08/09.md

1.8 KiB

በዚያን ቀን ይመጣል

“በዚያን ዘመን ይፈፀማል”

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ስለ ራሱ በራሱ ሥም ይናገራል፡፡ይሄንን በአሞፅ 4፤5 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡የአሞፅ ትርጉም “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚናገረው ይህንን ነው” ወይም “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ያለው ይሄንን ነው” (መጀመሪያ፤ሁለተኛና ሦስተኛ የሚለውን ይመልከቱ)

ራስ መንጨትንም በሁሉ ላይ አመጣለሁ

አንድ ሰው ራሱን የሚላጨው ሐዘን ላይ መሆኑን ለመግለፅ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ራሣችሁን እንደትላጩ ያደርጋችኋል” (ተምሣሌታዊ ድርጊትን ይመልከቱ)

ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ ለቅሶ

አንድ ልጅ ብቻ እንዳላቸውና ያ አንዲያ ልጃቸው እንደሞተባቸውየሚገልፅ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “አንድ ልጅ ብቻ ኖሯቸው ለእርሱ እንደሚያለቀሱ”(ቃላትን ሳይጠቀሙ ሃሣብን መግለፅ የሚለውን ይመልከቱ)

ፍፃሜውንም መራራ አደርገዋለሁ

አሰቃቂና መጥፎ ነገሮች በቀን ብርሃን መከናወናቸው ልክ ቀኑ ራሱ መራራ ጣዕም አንዳለው ዓይነት ተደርጎ ተነግሯል፡፡የአሞፅ ትርጉም“ በዚያን ወቅት የሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ ለታላቅ ሐዘን ይዳርጓችኋል፡፡”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)