am_tn/amo/07/12.md

1.1 KiB

በዘያም እንጀራን ብላ በዚያም ትንቢትን ተናገር

እዚህ ላይ “እንጀራን ብላ”የሚለው ቃል የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ትርጉሙም ገንዘብ ማግኘት ወይም አንድ ነገርን በመሥራት ለኑሮ የሚበቃ ነገር ማግኘትን ነው የሚያመለክተው፡፡የአሞፅ ትርጉም “እዚያ ሥፍራ ላይ ትንቢት ስለምትናገር ገንዘብ የሚከፍሉህን ሰዎች ፈልግ”ወይም “እዚያ ሥፍራ ላይ ትንቢት ተናገርና ምግብ ያቅርቡልህ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

የንጉሥ መቅደስና የመንግሥት ቤት ናትና

እዚህ ላይ“የንጉሥ መቅደስ” እና “የመንግሥት ቤት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ተመሳሳይ ሥፍራዎችን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ንጉሡ የሚያመልክበት አገር አቀፉ የመቅደስ ሥፍራ እዚህ ነው፡፡”