am_tn/amo/07/10.md

2.0 KiB

የቤቴል ካህን አሜስያስ

ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/አሜስያስ በቤቴል ውስጥ የቀረ ብቸኛ ካህን ነበር 2/አሜስያስ በቤቴል ውስጥ ለነበሩ ካህናት አለቃ ነበር

አሜስያስ

ይሄ የአንድ ሰው ሥም ነው፡፡(ሥሞች እንዴት ነው መተርጎም የሚኖርባቸው?የሚለውን ይመልከቱ)

አሞፅ በእሥራኤል ቤት መካከል አምፆብሃል

እዚህ ላይ“ቤት” የሚለው ቃል የሚወክለው “ሕዝቦችን” ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “አሞፅ እዚሁ በእሥራኤላውያን መካከል ሆኖ መጥፎ ነገርን እያሴረባችሁ ነው”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ )

ምድሪቱ ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም

እዚህ ላይ“ምድር” የሚለው ቃል የሚያመለክተው “ሕዝቦችን” ነው፡፡እዚህ ላይ “ሠላምን ማናጋት” የሚለው ሃሣብ የተገለፀው አሞፅ ካባድ እንደሆነ ግዑዝ ዕቃ እንደሆነና ምድሪቱ ለመሸከም እንዳቃታት ተደርጎ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “እርሱ የሚናገረው ቃል የሕዝቡን ሠላም ያናጋል”ወይም “የሚናገረው መልዕክት በሕዝቡ መካከል ችግር እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውንና ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ ይመልከቱ)

ኢዮርብዓም በሠይፍ ይሞታል

እዚህ ላይ“ሠይፍ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጠላቶችን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ጠላቶች ኢዮርብዓምን ይገድሉታል”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)