am_tn/amo/07/09.md

1.6 KiB

የይሥሐቅም የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤የእሥራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፤በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሠይፍ እነሣለሁ

እዚህ ላይ “ሠይፍ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጠላትን ነው፡፡ይሄ የራሱ በሆነ አገላለፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “የኢዮርብዓምን ቤት የሚያጠቃ ሠራዊት እልካለሁ፤እነርሱም የይሥሐቅን የኮረብታ መስገጃዎችና የእሥራኤልን ቤተ መቅደሶች ባድማ ያደርጋሉ”( ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃልን እና አድራጊ ግሥን ወይም ተካፋይ ያልሆነ የሚለውን ይመልከቱ )

ይሥሐቅ …እሥራኤል

እነዚህ ሁለቱም ቃላት የእሥራኤልን ቤት የሚያመለክቱ ናቸው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የይሥሐቅ ትውልድ”…“የእሥራኤል ሕዝብ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

የኢዮርብዓም ቤት

እዚህ ላይ “ቤት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ቤተሰብን ነው፡፡በአሞፅ 1፤1 ላይ እንዳደረጋችሁት ሁሉ ኢዮርብዓም የሚለውን ቃልንም ተርጉሙት፡፡የአሞፅ ትርጉም “ኢዮርብዓምና ቤተሰቡ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)