am_tn/amo/06/12.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ግሣፄን ያደርግ ዘንድ ሃሣባቸውን ወደ እርሱ እንዲሰበስቡ ለማድረግ አሞፅ ሁለት የበሰሉ ጥያቄዎችን ያቀርባል፡፡

ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይጋልባሉን?

አንድ ፈረስ ጉዳት ሳይደርስበት በዓለታማ ኮረብታዎች ላይ ሊጋልብ አይችልም፡፡አሞፅ እነዚህን ሁለት የበሰሉ ጥያቄዎችን የጠየቀው አድራጎታቸውን ለመገሰፅ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ፈረሶች በዓለታማ ኮረብቶች ላይ ሊሮጡ አይችሉም፡፡”(በሙያ የታገዘ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ )

በሬዎች በዚያ ላይ ያርሳሉን?

ሰው በዓለታማ ሥፍራ ላይ ሊያርስ አይችልም፡፡አሞፅ እነዚህን ሁለት ሪቶሪክ ጥያቄዎችን የጠየቀው አድራጎታቸውን ለመገሰፅ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ሰው በዓለታማ ሥፍራ ላይ በበሬ አያርስም፡፡”(በሙያ የታገዘ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ፍርድን ወደ ሀሞት ለውጣችኋል

ትክክለኛ የሆነ ነገርን የማዛባት ጉዳይ መሪዎች“ፍትህን ወደ ሐሞትነት”እንደለወጡ ተደርጎተነፃፅሯል፡፡የአሞፅ ትርጉም“ትክክለኛ የሆነ ነገርንታጣምማላችሁ” ወይም “ቅን ሰዎችን የሚጎዱ ሕጎችን ታወታላችሁ፡፡”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የፅድቅንም ፍሬ ወደ ሐሞት

ይሄ ከመጀመሪያው የዓረፍተ ነገር ክፍል ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ትክክለኛ ነገሮችን ማዛባት ሰዎች የፅድቅን ፍሬ በመውሰድ ወደ መራራ ጣዕም እንደለወጡትተደርጎ ተነፃፅሮ፡፡የአሞፅ ትርጉም “ትክክለኛ የሆነ ነገርን ታጣምማላችሁ ”ወይም “ትክክለኛ ነገር ያደረጉትን ሰዎች ትቀጣላችሁ”(ንፅፅርና ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሐማትና…ዓረባ

እነዚህ የከተማ ስሞች ናቸው፡፡(እነዚህን ስሞች እንዴት እንደምትተረጉሟቸው እዩ)

ዓረባን በኃይላችን ቀንድ ወሰድን አይደለንምን?

ሰዎቹ በራሣቸው ኃይል ከተማዋን እንደወሰዱዷትአፅንዖት ለመስጠት በጥያቄ መልክ ያቀርባሉ፡፡የአሞፅ ትርጉም “ዓረባን የያዝናት በራሣችን ጉልበት ነው” (በሙያ የታገዘ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)