am_tn/amo/06/11.md

1.3 KiB

ተመልከቱ

“ስሙ”ወይም “ትኩረታችሁን ወደዚህ አድርጉ”

ታላቁንም ቤት በማፍረስ፤ታናሹንም ቤት በመሰባበር ይመታል

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆኑ ትርጉሞች ያላቸው ናቸው፡፡“ትልቁ ቤት”እና “ትንሹ ቤት”በሚለው መካከል ያለው ንፅፅር ትርጉም ሁሉንም ቤቶች የሚመለከት ጉዳይ መሆኑን ነው፡፡(ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ታላቁንም ቤት ያፈርሳል

ይሄ በአድራጊ ግሥ ሊገለፅ ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም“ጠላት ትልቁን ቤት ወደ ፍርስራሽነት ይለውጠዋል፡፡”(አድራጊ ግሥንና ተካፋይ ያልሆነ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ፍርስራሽነት…ወደ አመድነት

ለእነዚህ ሐረጎች ሁለቱንም ቃላት መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

ታናሹንም ቤት በመሰባበር

ይሄ ሰዎች በገባቸው መረጃ አኳያ ሊገለፅ የሚችል ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ጠላቶች ትንሹን ቤት ወደ አመድነት ይለውጡታል፡፡” (ቃላትን ሳይጠቀሙ ሃሣብን በምልቶች(ሥነፅሑፋዊ) መግለፅ የሚለውን ይመልከቱ)