am_tn/amo/06/09.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር የእሥራኤልን ሕዝብ ለጠላቶቻቸው አሣልፎ በሚሰጥበት ወቅት ሊፈጠሩ ይችላሉ ብሎ የገመታቸውን ሁኔታዎች በአሞፅ 6፡9-10 ላይ ይገልፀዋል፡፡(ግምታዊ ሁኔታዎች የሚሉትን ይመልከቱ)

አሥር ሰዎች በአንድ ቤት ውስጥ ቢቀሩ እነርሱ ይሞታሉ

ይሄ የሚያመለክተው አሰቃቂ ነገር እንደሚከናወንና እነዚህ አሥር ሰዎች ለመደበቅ ወደ ቤት ውስጥ የሚገቡ መሆኑን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም“አሥር ሰዎች ቤት ውስጥ የሚደበቁ ቢሆኑም እንኳን እነርሱም ይሞታሉ፡፡”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውንና ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አጥንቱንም ከቤቱ ያወጡ ዘንድ የሰው ዘመድና አቃጣዩ ባነሱት ጊዜ በቤቱም ውስጥ ያለውን እስከ አሁን ድረስ ገና ሰው በአንተ ዘንድ አለን? ባለው ጊዜ…

የእነዚህ ቃላት ትርጉም ግልፅ አይደለም፡፡ለእነዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት 1/ “የሰዎቹ ቤተሰብ” የሚባለው ሰው “አካላቸውን ወስዶ” “ሬሣቸውን የሚያቃጥለውን” ሰው ሲሆን ይህ ሰው አሥሩ የቤተሰቡ አባላት ሕይወት ካለፈ በኋላ በቤት ውስጥ ተደብቆ ከነበረ ሰው ጋር እየተነጋገረ ነው ወይም 2/ “ሬሣቸውን ለመውስድ የሚመጣው ሰው”“የሰዎቹ የቅርብ ዘመድ”“ሬሣውን ከሚገንዘው ሰው የተለየ ሰው ነው”እርስ በእርሳቸውም በቤት ውስጥ ይነጋገራሉ፡፡የአሞፅ ትርጉም“የሰዎቹ የቅርብ ዘመዶች ሬሣዎቹን ወስደው ከቤቱ ውስጥ ከወጡ በኋላ ሬሣዎቹን የሚያቃጥለው ሰው ደግሞ ከእነርሱ ጋር አብሮ ይሄዳል…በቤት ውስጥ በነበሩበት ወቅት ቅርብ ዘመዳቸው የሆነው ሰው ሬሣዎቹን ለሚያቃጥለው ሰው “በአንተ ዘንድ አለን?”ብሎታል፡፡

ሬሣን ማቃጠል የሞተን የሰው አካል ማቃጠል ሬሣዎችን ማምጣት

“የሞተ አካልን መሰብሰብ”

የእግዚአብሔርን ሥም እንጠራ ዘንድ አይገባንምና ዝም በል ይለዋል

የዚህ ትርጉም ግልፅ አይደለም፡፡ይሄ ጥያቄውን የጠየቀው ሰው ፍርሃት እንደያዘውና የሚመልሰውም ሰው የእግዚአብሔርን ሥም በግድየለሽነት እንደሚጠራ ነው የሚያመለክተው፡፡ይህንን የሚያደርግ ከሆነ የእግዚአብሔርትኩረት ወደ እነርሱ በመሳብ በሕይወት እንዳይኖሩ ሊያደርጋቸውም ይችላል፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውንና ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ )