am_tn/amo/06/01.md

2.8 KiB

ተዘልለው ለተቀመጡ

“ተዘልለው የተቀመጡ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች ምቹ ሁኔታ ውስጥ ከመኖራቸው የተነሣ ስለ እግዚአብሔር ፍርድ ብዙም ትኩረት የማይሰጡ መሆኑን ነው፡፡

ምርጥ የሆነው አገር ውስጥ የሚኖሩ የተከበሩ ሰዎች

“በዚህ ታላቅ አገር ውስጥ የሚኖሩ የተከበሩ ሰዎች”የሚለው ቃል ምናልባትም እግዚአብሔር እነዚህ ሰዎች ስለራሣቸው ያላቸውን አስተሳሰብ በተመለከተ በምፀት የሚናገረው ነገር ሊሆን ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ምርጥ በሆነ አገር ውስጥ ምርጥ የሆንን ሰዎች ነን ብለው የሚያስቡ ሰዎች”

የእሥራኤልም ቤት ይመጣል

“ቤት” የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች እንደ አጠቃላይ መጠሪያ ነው፡፡በዚህ አውድ አንፃር የእሥራኤልን የዘር ሐረግ የሚመለከት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም“የእሥራኤል ነገድ እየመጣ ነው፡፡” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ሊረዳ መጣ

እዚህ ላይ“መጣ” የሚለው ቃል “ይሄዳል”ተብሎ ሊገለፅ ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ለመርዳት ይሄዳል” (መሄድና መምጣት የሚለውን ተመልከቱ)

ካልኔ

ይሄ የከተማ ሥም ነው፡፡(ሥሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ ተመልከቱ)

ከሁለቱ መንግሥታቶች ይልቅ የተሻሉ ናቸውን?

ታዋቂ የሆኑ ሰዎች ይህንን ጥያቄ ከሌሎች መንግሥታት ይልቅ የእሥራኤልና የይሁዳ መንግሥታት የተሻሉ ናቸው የሚለውን ሃሣብ አፅንዖት ለመስጠት ይጠቀሙበታል፡፡የአሞፅ ትርጉም “የእናንተ ሁለት መንግሥታት ከእነርሱ ይልቅ የተሻሉ ናቸው”(በሙያ የታገዘ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ድንበራችሁ ከድንበራቸው ይልቅ ይሰፋልን?

ታዋቂ የሆኑ ሰዎች ይህንን ጥያቄ ከሌሎች መንግሥታት ይልቅ የእነርሱ መንግሥታት የተሻሉ ናቸው የሚለውን ሃሣብ አፅንዖት ለመስጠት ይጠቀሙበታል፡፡የአሞፅ ትርጉም“ከእናንተ ይልቅ ድንበሮቻቸው ያነሱ ናቸው”ወይም “እነዚያ አገራት ከይሁዳና ከሰማርያ ይልቅ አነስተኞች ናቸው፡፡”(በሙያ የታገዘ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)