am_tn/amo/05/25.md

2.5 KiB

እሥራኤል ሆይ መሥዋዕትን አቅርባችሁኛልን?

የዚህ ትርጉም ሊሆኑ የሚችሉ 1/እግዚአብሔር ይሄንን ጥያቄ ያነሣው መሥዋዕትን ባለማቅረባቸው ሊገስፃቸው ፈልጎ ነው ወይም ደግሞ 2/እግዚአብሔር ይሄንን ጥያቄ ያነሣው ከእርሱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ መሥዋዕት እጅግ አስፈላጊው ነገር እንዳልሆነ ሊያሳስባቸው ፈልጎ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም“እሥራኤል ሆይ መሥዋዕት ልታመጡልኝ አያስፈልጋችሁም ነበር” (በሙያ የታገዘ ጥያቄ የሚለውን ተመልከቱ)

አቅርባችሁኛልን?

እግዚአብሔር እየተናገራቸው ያሉትን እሥራኤላውያን የሚናገራቸው ልክ በበረሃ ሲጓዙ ከነበሩት ወገኖች ጋር እንደነበሩ አስመሰሎ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የቀደሙት አባቶቻችሁ አምጥተውልኛል?” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ )

የእሥራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤት ወስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ሌላው ሥም ነው፡፡በዚህ አውድ ውስጥ ይሄ የሚያመለክተው የእሥራኤልን ትውልዶች ነው፡፡በአሞፅ 5፡1 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡የአሞፅ ትርጉም“እናንተ የእሥራኤል ቤት ሆይ” ወይም “እናንተ የእሥራኤል ነገድ የሆናችሁ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

የሞሎክን ድንኳንና የሬፋን ኮከብ አነሳችሁ

እዚህ ላይ“ኮከብ አነሳችሁ”የሚለው ቃል እነርሱን ማምለካቸውን የሚያመለክት ነው፡፡“የሞሎክን ኮከብ አነሳችሁ …የሬፋንንንም”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ሞሎክ …ሬፋን

እነዚህ የሁለት ጣዖታት ሥሞች ናቸው፡፡ሰዎች እነርሱን እንዲወክሏቸው ጣዖታትን ቀርፀዋል፡፡(ሥሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ ተመልከቱ)

ሬፋን

አንዳንድ ቅጂዎች ይሄንን“ኪዩም”ብለው ይተረጉሙታል፡፡