am_tn/amo/05/18.md

2.4 KiB

የእግዚአብሔር ቀን እንዲመጣ ለምን ትናፍቃላችሁ?

እግዚአአብሔር ይሄንን ጥያቄ የእግዚአብሔር ቀን በፍጥነት እንዲመጣ በመናፈቃቸው ሊገስፃቸው የተናገረው ነው፡፡ይሄ እንደ መግለጫ ሊገለፅ ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “የእግዚአብሔርን ቀን ናፈቃችሁ” ወይም “የእግዚአብሔርን ቀን መናፈቅ የለባችሁም”(በሙያ የታገዘ ጥያቄ የሚለውን ተመልከቱ)

ጨለማ ነው እንጂ ብርሃን አይሆንም

እዚህ ላይ“ጨለማ”የሚያመለክተው ጥፋት የሚከሰትበትን ወቅት ሲሆን “ብርሃን”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ደግሞ መልካም ጊዜ የሚከሰትበትን ወቅት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የጨለማና የጥፋት ጊዜ እንጂ የብርሃንና የበረከት ጊዜ አይሆንም”ወይም “በዚያን ዕለት ጥፋት እንጂ በረከት አይኖርም”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በውኑ የእግዚአብሔር ብርሃን ሣይሆን ጨለማ አይደለምን?

ይሄ ጥያቄ አፅንዖት የሚሰጠው መጥፎ ነገሮች የሚከናወኑ መሆኑን ነው፡፡እንደ መግለጫ ሊገለፅ ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “የእግዚአብሔር ቀን በእርግጥም ጨለማ እንጂ ብርሃን አይሆንም”ወይም “በእግዚአብሔር ቀን በእርግጥ መልካም ያልሆኑ ነገሮች ይከሰታሉ”(በሙያ የታገዘ ጥያቄ የሚለውን ተመልከቱ)

ድቅድቅ ጨለማ አንጂ ብርሃን አይሆንም

“በውኑ የእግዚአብሔር ቀን”የሚሉትን ቃላት ከቀደመው ዓረፍተ ነገር መረዳት ይቻላል፡፡ከዚህ በፊት እንደነበረው ጥያቄ በእግዚአብሔር ቀን አሰቃቂ ነገሮች፤መልካም ያልሆኑ ነገሮች እንደሚከሰቱ አፅንዖት ሰጥቶ ይናገራል፡፡ይሄ አንደ መግለጫ ሊነገር ይችላል፡፡“መልካም ነገር ሣይሆን ክፉ ነገሮች የሚከሰቱበት ጊዜ ይሆናል፡፡”(በሙያ የታገዘ ጥያቄንና ተመሣሣይነት የሚለውን ተመልከቱ)