am_tn/amo/05/14.md

2.4 KiB

መልካሙን እሹ፤ ክፉውን ነገር ተፀየፉ

“ክፉ ሥራዎችን ተፀየፉ፤መልካም የሆኑ ሥራዎችን ውደዱ” “መልካም” እና “ክፉ”መልካም የሆኑ ድርጊቶችንና ክፉ የሆኑ ድርጊቶችን ይወክላሉ፡፡

በከተማው አደባባይ ፍትህን አድርጉ

እዚህ ላይ “ፍትህን አድርጉ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ፍትህ ስለመረጋገጡ እርግጠኛ መሆንን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም“በከተማው አደባባይ ላይ ፍትህ መከናወኑን እርግጠኛ ሁኑ” ወይም “በእነዚህ የከተማ አደባባዮች ላይ ዳኞቹ ፍትህን ስለ ማድረጋቸው እርግጠኞች ሁኑ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በከተማው አደባባይ ላይ

የከተማው የአደባባይ ደጆች ወፍራምና ጠንካራ በመሆናቸው ሰዎች ከሞቃቱ የፀሐይ ትኩሣት ራሣቸውን የሚያስጠልሉበት ከመሆኑም ባሻገር የንግድ ልውውጥ የሚደረግባቸውና ዳኝነት የሚሰጥባቸው ሥፍራዎች ነበሩ፡፡ የአሞፅ ትርጉም “በፍርድ አደባዮቻችሁ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ )

የዮሴፍ ቅሬታ

እዚህ ላይ “ቅሬታ”የሚለው ቃል ሌሎቹ ከተገደሉና በምርኮ ከተወሰዱ በኋላ በእሥራኤል አገር ውስጥ የሚቀሩትን ሰዎች የሚያመለክት ነው፡፡እዚህ ላይ “ዮሴፍ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው አብዛኛዎቹ የዮሴፍ የዘር ሐረግ የሆኑትን በሰሜን ክፍል ያለውን የእሥራኤል ግዛት ነው፡፡ በአሞፅ 5፤6 ላይ “የዮሴፍ ቤት”የሚለውን ቃል እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡የአሞፅ ትርጉም “እስከ አሁን ድረስ በሕይወት ያሉ የዮሴፍ የዘር ሐረጎች”ወይም “በሕይወት የተረፉ እሥራኤላውያን” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)