am_tn/amo/05/06.md

3.1 KiB

እግዚአብሔርን ፈልጉት

እዚህ ላይ “እግዚአብሔርን ፈልጉት” የሚለው ቃል ከእርሱ ዕርዳታን መፈለግን የሚያመለክት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “እግዚአብሔር እንዲረዳችሁ ጥሩት”ወይም “እኔ እግዚአብሔርን ለዕርዳታ ጠይቁኝ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ እሣት ይነሳል

“እንደ እሣት ይነሳል”የሚለው ቃል የሚወክለው እሣት ነገሮችን እንደሚያጠፋ እንዲሁ የነገሮችን መውደም ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም ተነፃፃሪ”

የዮሴፍ ቤት

ይሄ ሐረግ ለዮሴፍ የዘር ሐረግ እንደ ሌላ ስም የተሰጠ ነው፡፡እዚህ ላይ የሚያመለክተው አብዛኛው የዘር ሐረጋቸው ከዮሴፍ ትውልድ የሆኑትንና በሰሜኑ የእሥራኤል ግዛት የሚገኙትን ነገዶች ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የዮሴፍ ትውልዶች”ወይም “እሥራኤል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ይበላል

“እርሱ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው እሣቱን ሲሆን “ይበላል” የሚለው ቃል የሚመለክተው ደግሞ ሁሉንም ነገር ፈፅሞ የሚያጠፋ መሆኑን ነው፡፡እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር የሚያጠፋ መሆኑን ለማመልከት እሣት ሁሉንም ነገር ከማጥፋቱ ጋር ተነፃፅሯል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ሁሉን ነገር ያጠፋል”ወይም “ሙሉ በሙሉ ያጠፋል”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሚያቆመው ሰው አይኖርም

“የሚያቆመው አይኖርም”ወይም “ሁሉንም ነገር ለማጥፋት የሚያቆመው ነገር አይኖርም”

ፍርድን ወደ እሬት ነገር ለወጡ

እዚህ ላይ “እሬት”የሚለው ቃል የሚወክለው ሰዎችን የሚጎዳ ድርጊትን ሲሆን “ፍርድን ወደ እሬት ነገር ለወጡ”የሚለው ቃል ደግሞ መልካም ነገርን ከማድረግ ይልቅ ሰዎችን የመጉዳትን ሃሣብ የሚያመለክት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ፍትሃዊ የሚመስል ነገርን እያደረጉ እነርሱ ግን ሰዎችን ይጎዳሉ”ወይም “ትክክለኛ የሆነውን ነገር እየተቃወሙ ከዚያ በተቃራኒው ሰዎችን የሚጎዳ ነገርን ይሰራሉ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ፅድቅንም በምድር ላይ ይጥላሉ

ይሄ የሚያመለክተው ፅድቅን እንደማይረባ ነገር መቁጠራቸውን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ፅድቅን አስፈላጊ እንዳልሆነ ቆሻሻ ነገር መቁጠር”ወይም “ፅድቅ የሆነውን ነገር ትፀየፋላችሁ”(ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)