am_tn/amo/05/04.md

1.4 KiB

እኔን ፈልጉኝ

እዚህ ላይ“ፈልጉኝ”የሚለው ቃል ወደ ቤቴል በመሄድ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው መጠየቅን የሚያመለክት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ዕርዳታ ለመሻት ወደ ቤቴል አትሂዱ”(ምሣሌያዊ አነጋገርን ይመልከቱ)

ወደ ጌልጌላም አትግቡ

“እና ወደ ጌልጌላ አትግቡ”

በእርግጥ ጌልጌላ በምርኮነት ትወሰዳለች

እዚህ ላይ “ጌልጌላ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የጌልጌላን ሕዝብ ሲሆን “በምርኮነት መወሰድ” የሚለው ቃል ደግሞ የሚያመለክተው በምርኮኛነት ተይዞ መወሰድን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም“በእርግጥ ጌልጌላ በምርኮነት ትወሰዳለች”ወይም “በእርግጥም ጠላቶቻችሁ የጌልጌላን ሕዝብ በኃይል በመያዝ ይዘዋቸው ይሄዳሉ፡፡”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀት የሚለውን ይመልከቱ)

ቤቴልም ከንቱ ትሆናለች

እዚህ ላይ “ከንቱ ትሆናለች”የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጥፋቷን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ቤቴል ፈፅሞ ትጠፋለች”ወይም “ጠላቶች ቤቴልን መሉ ለሙሉ ያወድሟታል”(ምሣሌዊ አነጋገርን ይመልከቱ)