am_tn/amo/04/12.md

2.4 KiB

ሃሣብን ማያያዝ

እግዚአብሔር ለእሥራኤል ሕዝብ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

አምላካችሁን ለመገናኘት ተዘጋጁ

እግዚአብሔር ይህንን የሚያደርገው በእሥራኤል ሕዝብ ላይ ፍርድ እንደሚፈርድባቸው ለማስጠንቀቅ ነው፡፡(መጀመሪያ፤ሁለተኛና ሶስተኛ አካልና )

እነሆ ተራረሮችን የሠራ …የልቡንም ሃሣብ የሚገልፅ..ስሙ…ነው

እዚህ ላይ አሞፅ ስለ እግዚአብሔር እንደሚናገር ወይም እግዚአብሐር ስለራሱ እንደሚናገር ግልፅ አይደለም፡፡እግዚአብሔር ስለ ራሱ የሚናገር ከሆነ “እኔ” ወደሚሉ ቃላት ሊተረጎም ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “እኔ ተራራሮችን የምሰራ…..ሃሣቤን የምገልፅ…ስሜ …. ነው፡፡”(መጀመሪያ፤ሁለተኛና ሶስተኛ አካልና በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትየሚለውን ይመልከቱ )

ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ

ከዚህ ጋር ሊሄዱ የሚችሉ ትርጉሞች 1/እግዚአብሔር የቀን ብርሃን እያለ ከባድ ደመና በማምጣት ቀኑን ድቅድቅ ጨለማ ሊያደርገው ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ማለዳን ጨለማ ሊያደርግ ይችላል፡፡”ወይም 2/እግዚአብሔር ቀናት በአስቸኳይ እንዲያልፉ በማድረግ እያንዳንዱ ቀን ጨለማ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ማለዳና ምሽት ያደርጋል”

በምድር ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ

እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ ገዢ እንደመሆኑ በምድር ከፍታዎች ላይ የሚራመድ እንደሆነ ይናገራል፡፡የአሞፅ ትርጉም “በምድር ሁሉ ላይ ይገዛል”ወይም “በምድር ላይ የሚገኙትንና ከፍታ ያላቸውን ቦታዎች እንኳን ይገዛል፡፡”(ምሣሌያዊን አነጋገርን ይመልከቱ)

ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው

ሙሉ ስሙን በማወጅ እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች እንደሚፈፅም ይናገራል፡፡ቋንቋችሁ ሰዎች ይህንን እንዲያደርጉ የሚያደርግበት መንገድ ሊኖረው ይችላል፡፡