am_tn/amo/04/10.md

3.7 KiB

በግብፅ እነደነበረው ቸነፈርን ሰደድኩባችሁ

“በግብፅ ላይ እንዳደረግኩት እንዲሁ በእናንተም ላይ ቸነፈርን ላክሁ”ወይም “በግብፅ ላይ ቸነፈርን እንደላክሁ እንዲሁ በእናንተም ላይ ቸነፈርን እልካለሁ”

ቸነፈርን ላክሁባችሁ

“በእናንተ ላይ አሰቃቂ ነገር እንዲሆንባችሁ አደረግኩ”

ጎበዛዝታችሁን በሠይፍ ገደልኩ

እዚህ ላይ“በሠይፍ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጦርነትን ነው፡፡እግዚአብሔር ጠላቶች እንዲነሱባቸውና እንዲዋጉዋቸው በማድረግ በሕይወት እንዳይኖሩ አደረጓቸው፡፡አሞፅ ትርጉም“ጠላቶቻችሁ በጦርነት ወቅት ሰዎቻችሁን እንዲገድሉ አደረግኳቸው፡፡” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ፈረሶቻችሁን ሁሉ በመማረክ ይዘው ሄዱ

እግዚአብሔር ጠላቶቻቸው ፈረሶቻቸውን እንዲወስዱ ማድረጉን ልክ ራሱ እንደፈፀመው ዓይነት አስመስሎ ይናገራል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ጠላቶቻችሁ ፈርቸችሁን እንዲወስዱባችሁ አደረግኩ፡፡”

የሠፈራችሁንም ግማት ወደ አፍንጫችሁ እንዲወጣ አደረግኩ

ግማት መጥፎ የሆነ ሽታ ነው፡፡ግማቱ እስከ አፍንጫቸው ድረስ መምጣቱ የሚያመለክተው ፈፅሞ ደስ የማይል ነገር እያሸተተቱ መሆናቸውን ነው፡፡ሽታው የሚመጣው ከሞቱ ሰዎች አካል እነደሆነ በግልፅ ያመለክታል፡፡የአሞፅ ትርጉም “በሠፈራችሁ ውስጥ ደስ የማይል የሞቱ ሰዎችን አካላት እንድታሸቱ አደረግኳችሁ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ከእሣት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ

እዚህ ላይ እግዚአብሔር የሚናገረው በዚያ በጦርነትና በቸነፈር ወቅት ልክ አንድ ሰው በትርን ከእሣት ጎትቶ እንደሚያወጣ በሕይወት ተርፈው ያሉትን ሰዎች የሚመለከት ነው፡፡(አንድ ሰው ከእሣት ውስጥ ጎትቶ እንደሚያወጣው በትር አንዳንዶቻችሁ በሕይወት ቆያችሁ፡፡) (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ እኔ አልተመለሳችሁም

ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ራስን ለእርሱ እንደገና ፈፅሞ ለእግዚአብሔር ማስገዛትን ነው፡፡ይሄንን በአሞፅ 4፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡የአሞፅ ትርጉም“ራሳችሁን እንደገና ፈፅሞ አልተገዛችሁልኝም፡፡” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

የተናገረው ነገር እውነት መሆኑን ለመግለፅ እግዚአብሔር በራሱ ሥም ይናገራል፡፡እነዚህን ቃላት በአሞፅ 2፤11 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ጌታ እግዚአብሔር የሚናገረው ይሀንን ነው”ወይም “ይህንን የተናገርኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ”(መጀመሪያ፤ሁለተኛና ሶስተኛ አካል)