am_tn/amo/04/06.md

3.1 KiB

ሐሣብን ማያያዝ

እግዚአብሔር ለእሥራኤል ሕዝብ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

የጥርስ ማጥራትንአደረግኩላችሁ

እዚህ ላይ የጥርስ ማጥራት የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጥርስን ሊያቆሽሽ የሚችል ምግብ በአፍ ውስጥ አለመግባቱን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “እንድትራቡ አደረግኋችሁ” ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

እንጀራን ማጣት

“እንጀራን ማጣት” ሰጠኋችሁ የሚለው ቃል እንጀራ እንዲያጡ ምክኒያት እንደሚሆንባቸው መግለፁ ሲሆን “እንጀራ”የሚለው ቃል ደግሞ የሚያመለክተው በአጠቃላይ የምግብ ዘርን ነው፡፡

ወደ እኔ አልተመለሳችሁም

ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ራስን እንደገና ለእርሱ ማስገዛትን ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “እንደገና ለእኔ አልተገዛችሁም” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከቱ)

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

የተናገረው ነገር እውነት መሆኑን ለመግለፅ እግዚአብሔር በራሱ ሥም ይናገራል፡፡ይናገራል፡፡እነዚህን ቃላት በአሞፅ 2፤11 ላይ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡“ጌታ እግዚአብሔር የሚናገረው ይሄንን ነው”ወይም “ይሄንን የተናገርኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ”(መጀመሪያ፤ሁለተኛና ሶስተኛ አካል)

ዝናብም ከለከልኳችሁ

“በሰብላችሁ ላይ ዝናብ እንዳይዘንብ ከለከልኩ”

መከርን ለመሰብሰብ ገና ሶስት ወራት ሲቀሩ

ሕዝቡ ዝናብ እንደሚያስፈልጋቸው በግልፅ ሊነገር ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “መከር ለመሰብሰብ ገና ሶስት ወራት በቀረበት ወቅት ሰብሎቻችን ዝናብ ያስፈልጋቸው ነበር” (በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በአንዱ ወገን ዝናብ ዘንቧል

ይሄ በአድራጊ ግሥ ሊገለፅ ይችላል፡፡“አንዱ ወገን”የሚለው ቃል የሚወክለው ማንኛውንም የተወሰነየመሬት ክፍል ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “በቁራጭ መሬት ላይ ዘነበ”ወይም “በተወሰኑ የመሬት ክፍሎች ላይ ዘነበ” (አድራጊ ግሥን ወይም ተካፋይ ያልሆነ የሚለውን ይመልከቱ)

ዝናብ ያልዘነበበት ምድር

ይሄ የሚያመለክተው ዝናብ ያልዘነበበትን ማንኛውንም ሥፍራ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ዝናብ ያልዘነበበት የተወሰ የመሬት ክፍል” (የመጀመሪያ ሥም(ሰዋሰው) ሐረጎች የሚለውን ይመልከቱ)