am_tn/amo/04/04.md

3.6 KiB

ሃሣብን ማያያዝ

እግዚአብሔር ለእሥራኤላውያን መናገሩን ይቀጥላል

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሔር በቁጥር 4 ላይ አጠቃላይ የሆኑ ትዕዛዛትን የሚሰጥ ቢሆንም ይህንን የሚያደርገው ግን መቆጣቱን ለመግለፅ ነው፡፡

ወደ ቤቴል ሄዳችሁ ኃጢአትን ሥሩ፤ወደ ጌልጌላ ሄዳችሁ ኃጢአትን አብዙ

ሰዎች መሥዋዕትን ለማቅረብ ወደ ቤቴልና ወደ ጌልጌላ የሚሄዱ ቢሆንም ይሄንን የሚያከናውኑት ግን ኃጢአትን በመፈፀም ጭምር ነበር፡፡እግዚአብሔር ይሄንን ትዕዛዝ የሚያስተላልፈውእነዚህን ተግባራት በመፈፀማቸው በእነርሱ ላይ ቁጣውን ለመግለፅ ነው፡፡እነዚሀ ትዕዛዛት በመግለጫ መልኩ ሊገለፁ ይችላሉ፡፡የአሞፅ ትርጉም “እናንተ ወደ ቤቴል የምትሄዱት ለአምልኮ ቢሆንም ኃጢአትን ታደርጋላችሁ፡፡አምልን ለማድረግ ወደ ጌልጌላ ትሄዳላች የምትሄዱት ግን የበለጠ ኃጢአትን ለማድረግ ነው፡፡”(ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

በየማለዳውም መሥዋዕታችሁን፤በየሦስተኛውም ቀን አሥራታችሁን አቅርቡ…በፈቃዳችሁም የምታቀርቡትን አውጁና አውሩ

እግዚአብሔር ይህንን ትዕዛዝ የሚያስተላልፈው ምንም እንኳን እነዚህን መልካም የሚመስሉ ነገሮችን ቢያደርጉም በሌላ በኩል ኃጢአት መሥራታቸውን ባለማቋረጣቸው ነው፡፡እነዚህ ትዕዛዛት እንደ መገለጫ ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡የአሞፅ ትርጉም“መሥዋታችሁን አምጡ …በየሶስተኛውም ቀናት የምሥጋና መሥዋዕትን ሰው፤የምታቀርቡትንም አውጁና አውሩ”(ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

በየሶስተኛውም ቀናት

ከዚህ ጋር ሊስማሙ የሚችሉ ትርጉሞች 1/በሶስተኛው ቀን ወይም 2/በየሶስት ቀናት፡፡ እሥራኤላውያን አሥራታቸውን በየሶስት ዓመቱ ያወጡ ስለነበረ አንዳንድ ቅጂዎች “በየሶስት ዓመት”ይሉታል፡፡

አውጁት

“ከእነርሱ የተነሣ ኩሩ”

እናንተ የእሥራኤል ሕዝብ ሆይ ይሄ ያረካችኋል

እግዚአብሔር በሚሰጡት ሥጦታና በሚሰውት መሥዋዕት ስለሚኩራሩ ይገስፃቸዋል፡፡እግዚአብሔር ደስ ይለዋል ብለው ቢያስቡም እርሱ ግን ደስ አልተሰኘባቸውም፡፡የአሞፅ ትርጉም “የእሥራኤል ሕዝብ ሆይ ይሄ ያስደስታችኋል እኔን ግን አያስደስተኝም”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና ግልፅ ያልሆነ መረጃን ይመልከቱ)

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

የተናገረው ነገር እውነት መሆኑን ለመግለፅ እግዚአብሔር በራሱ ሥም ይናገራል፡፡በአሞፅ 2፤11 ላይ ይሄንን ተመሳሳይ ሐረግ እንዴት እንደተረጎማችሁት ተመልከቱ፡፡የአሞፅ ትርጉም “ጌታ እግዚአብሔር የሚናገረው ይህንን ነው”ወይም “ይህንን የተናገርኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ”(መጀመሪያ፤ሁለተኛና ሶስተኛ አካል)