am_tn/amo/04/01.md

3.0 KiB

እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ ፤እናንተ በሰማርያ ተራሮች ላይ የምትኖሩ

አሞፅ በሰማርያ ለምትኖር እሥራኤላዊ ሴት ውስጥ ከጠገቡ ላሞች ጋር በማመሳሰል ይነግራታል፡፡የአሞፅ ትርጉም “በሰማርያ ተራራ ላይ የምትኖሩ እናንተ ባለፀጋ የሆናችሁ ሴቶች፤ ከጠገቡ የባሳን ላሞች ጋር የምትመሳሰሉ”(ምሣሌያዊ አነጋገርን ይመልከቱ)

ድሆችን የምትጨቁኑ

“ድሆች”የሚለው ቃል ድሃ የሆኑ ሰዎችን የሚያመለክት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “እናንተ ድሃ ሰዎችን የምትጨቁኑ”(አሕፅሮተ ቅፅል ሥምን ይመልከቱ)

ችግረኞችን የምታስጨንቁ

“ማስጨነቅ”የሚለው ቃል ሰዎችን መልካም ባልሆነ አያያዝ መያዝን የሚያመለክት ነው፡፡“ችግረኞች”የሚለው ሐረግ ዕርዳታ የሚሹ ሰዎችን የሚያመለክት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “እናንተ ችግረኞችን የምታስጨንቁ”ወይም “የተቸገሩ ሰዎችን የምትጎዱ”(ምሣሌያዊ አነጋገርና አሕፅሮተ ቅፅል ሥም የሚለውን ይመልከቱ)

ጌታ እግዚአብሔር በቅዱስነቱ ምሏል

ይሄ ማለት እግዚአብሔር አንድ ነገር ለማድረግ ቃል መግባቱንና የገባውን ቃል የሚፈፅመው ቅዱስ በመሆኑ ነው ማለት ነው፡፡

እነሆ ቀን በእናንተ ላይ ይመጣል

“እናንተ”የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሰማርያ ውስጥ የሚገኙ የእሥራኤል ሴቶችን ሲሆን ወንዶቹንም ያካትታል፡፡

እነርሱ እናንተን በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን ይመጣል

ቀናቶቹ ራሣቸው ጥቃት የሚፈፀሙባቸው ይመስል በሕዝቡ ላይ ክፉ ነገሮች እንደሚመጡ ይናገራል፡፡“እነርሱ”የሚለው ቃል ጠላቶቻቸውን የሚያመለክት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ጠላቶቻችሁ እናንተን በመጠንቆ የሚወስዱበት ጊዜ ይመጣል” (ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በወጥመድ ጠምደው ይወስዷችኋል፤ቅሬታችሁንም በዓሣ መያዣ መንጠቆ ይይዛችኋል

በመሠረቱ እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሣሣይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን ሰዎች ልክ እንደ ዓሣ በሰዎች ሊያዙ እንደሚችሉ አፅንዖት የሚሰጥ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ልክ እንስሳ እንደሚያዝ ይዘው ይወስዷችኋል”ወይም ደግሞ “ክፉኛ ያሸንፏችሁና በጭካኔ እየጎተቱ ይወስዷችኋል”(ንፅፅርንን እና ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)