am_tn/amo/03/15.md

2.2 KiB

የክረምት ቤትና የበጋ ቤት

አንዳንድ ባለፀጋ የሆኑ ሰዎች በአንደኛው ቤታቸው ውስጥ በክረምት ወራት የሚኖሩበት ሲሆን በሁለተኛው ቤታቸው ውስጥ ደግሞ የበጋ ወራት በሚሆንበት ወቅት ይኖሩበታል፡፡ይሄ ማንኛውንም የክረምትና የበጋ ቤቶችን ያመለክታል፡፡የአሞፅ ትርጉም“የመጀመሪያ ሥም(ሰዋሰው) ሐረጎች የሚለውን ተመልከቱ ”

በዝሆን ጥርስ የተሰሩት ቤቶች ይጠፋሉ

እግዚእብሔር ቤቶቹ ሕይወት እንዳላቸውና ሟቾች እንደሆኑ በመቁጠር ይናገራቸዋል፡፡የአሞፅ ትርጉም “በዝሆን ጥርስ የተሰሩት ቤቶች ይጠፋሉ”(ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)

በዝሆን ጥርስ የተዋቡ ቤቶች

“በዝሆን ጥርስ የተዋቡ ቤቶች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በየግድግዳዎቻቸውና በቤት ቁሣቁሶቻቸው ላይ በዝሆን ጥርስ የተዋቡትን ነገሮች ነው፡፡የዝሆን ጥርስ እጅግ ውድ ከመሆኑ የተነሳ በዝሆን ጥርስ የተዋቡ ቁሣቁሶች ያሏቸው ሰዎች ባለፀጋ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡

የዝሆን ጥርስ

የግዙፍ እንስሳት ጥርሶችና ቀንዶች

ታላላቅ ቤቶችም ይፈርሳሉ

“ትላልቅ ቤቶች አይኖሩም”እዚህ ላይ “ይፈርሳሉ”የሚለው ቃል የሚወክለው ፈፅመው ይደመሰሳሉ የሚለውን ነው፡፡

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እውነት ስለመሆኑ ማረጋገጫ ለመስጠት ራሱን በተመለከተ በራሱ ሥም ይናገራል፡፡“እግዚአብሔር የተናገረው ይህንን ነው” ወይም “ሥላሴዎችየተናገሩት ይህንን ነው፡፡” (የመጀመሪያ፤ሁለተኛና ሶስተኛ አካል የሚለውን ይመልከቱ)