am_tn/amo/03/11.md

2.5 KiB

ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

ይሄንን ለማን ለመናገር እንደፈለገ በግልፅ ማስቀመጥ ይቻላል፡፤የአሞፅ ትርጉም “ስለሆነም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሠማርያ ለሚኖሩ እሥራኤላውያን የሚናገረው ይህንን ነው፡፡”

ምድሪቱን ጠላት ይከብባታል፡፡

ምድሪቱ በጠላት ትከበባለች

አዳራሾችዋን ይበዘብዛሉ

“በአዳራሾቻችሁ ውስጥ የሚገኙትን ነገሮች ሁሉ ይሰርቃሉ፡፡”

እረኛ ከአንበሣ አፍ እንደሚድን…እንዲሁየእሥራኤልን ሕዝብ ይታደጋል

ጌታ እግዚአብሔር የእሥራኤልን ሕዝብ መታደግ አንድን እንስሳ ከአንበሣ አፍ ለማዳን ሊሳካ ካልቻለ ጥረት ጋር ያነፃፅረዋል፡፡በከፊል ይድናሉ፡፡(ተነፃፃሪነት የሚለውን ይመልከቱ)

እረኛ ከአንበሣ አፍ ውስጥ ሁለት እግሮችን ወይም የጆሮ ጫፍን ብቻ እንደሚያድን

እዚህ ላይ እረኛው የእንስሳውን ሙሉ አካል ለማስጣል ሙከራ ስለማድረጉ ነው የሚገልፀው፡፡የአሞፅ ትርጉም “እረኛው እንስሳውን ከአንበሣ አፍ ለማስጣል የሞከረ ቢሆንም ለማዳን የቻለው ግን ሁለት እግርና የጆሮን ጫፍ ብቻ ነው፡፡”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና ውስጣዊ ወይም ግልፅ ያልሆነ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ እረኛው … አንበሳው

እዚህ ላይ“እረኛው” እና “አንበሳው”የተሰኙት ሐረጎች ማንኛውንም እረኛና አንበሳ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡(የመጀመሪያ ሥም(ሰዋሰው) ሐረጎች የሚለውን ተመልከቱ)

የአልጋ ማዕዘን ብቻ ይቀርላቸዋል

ይሄ ሐረግ ሙሉ በሙሉ ሊድኑ የማይችሉ መሆኑን ነው የሚያሣየው፡፡ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የሚሰረቅ ይሆናል፡፡ይህንን ክፍል በዕብራይስጥ ቋንቋ ለመረዳት አስቸጋሪ ሲሆን አንዳንድ የዘመኑ የትርጉም ቅጂዎች ግን ለየት ባለ መንገድ ይተረጉሙታል፡፡

መከዳ

ይሄ ሰው ሊጋደምበት የሚልና ልስላሴ ያለው ትልቅ ወንበር ነው፡፡