am_tn/amo/03/09.md

2.6 KiB

ተሰብሰቡ

ይሄ ትዕዛዝ በአዛጦንና በግብፅ ስላሉት ጠላቶች የተሰጠ ትዕዛዝ ነው፡፡

ይሄ የእግዚአብሔርአዋጅ ነው

“እግዚአብሔር ያወጀው ይህንን ነው”ወይም “ያህዌ በለሆሳስ ያለው ይህንን ነው”ይሄ ሐረግ በሌላው መልዕክት ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ እውነተኛ መሆኑን የሚገልፅ ነው፡፡

በመካከልዋም ያለውን ግፍ ተመልከቱ

“በመካከልዋም”የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰማርያን ከተማ ነው፡፡ከተማዎች አብዛኛውን ጊዜ ይጠሩ የነበሩት በሴት ፆታ ነበር፡፡(ግዑዝ ነገሮች ሕይወት እንዳላቸው ተደርገው ሲገለፁ የሚለውን ይመልከቱ)

በመካከልዋም ያለውን ግራ መጋባት ተመልከቱ

እዚህ ላይ “በመካከልዋም ያለውን ግራ መጋባት ተመልከቱ” የሚለው ቃል በዚያ በሚካሄደው ጦርነትና አመፅ መካከል ሰዎች ያለባቸውን ፍርሃት ለማመልከት ነው፡፡“ግራ መጋባት ”የሚለው ቃል ግልፅ የሆነ ትርጉም እንዲይዝ ለማድረግ በግሣዊ ሐረግ መተርጎም ይቻላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “በሰማርያ የሚገኙ ሰዎች እንዴት እንዳመፁ”ወይም “የሰማርያ ሰዎች እርስ በእርሳቸው እንዴት እንደተዋጉ”(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀት፤ግልፅ የሆነ መረጃ የሚለውንና አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)

ምን ዓይነት ነው?

“በውስጧ ያለው ጭቆና”የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው በሰማርያ ውስጥ ሰዎችን ስለሚጨቁኑ መሪዎች ነው፡፡የሆነው “ጭቆና”የሚለው አሕፅሮተ ሥም “መጨቆን”ወይም “ለሥቃይ መዳረግ”ተብሎ ሊገለፅ ይችላል፡፡ (አሕፅሮተ ሥም የሚለውን ይመልከቱ)

ትክክለኛ የሆነ ነገርን ማድረግ አያውቁበትም

እዚህ ላይ “አመፅና ጥፋት”የሚለው ቃል ነገሮችን በአመፅና በማውደም መንጠቅን የሚያመለክት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ከሌሎች ላይ በአመፅ የነጠቁትን ገሮች ያከማቻሉ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)