am_tn/amo/03/01.md

3.7 KiB

እንዲህ ይላል

“ይህንን መልዕክት አዳምጡ”ወይም “ይሄንን መልዕክት ስሙ”

እግዚአብሔርእናንተን በመቃወም ተናግሯል… በአጠቃላይ ወገኑን በመቃወም

“እግዚአብሔር ስለ እናንተ የተናገረው ይሄ ቃል … በአጠቃላይ ስለ ወገኑ”ወይም “እግዚአብሔር ለእናንተ ያለው መልዕክት….ስለ ወገናችሁ በአጠቃላይ”

እናንተ የእሥራኤል ልጆች ሆይ …. ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ ወገን ሁሉ

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ ስለሆኑ ሁለት ሕዝቦችን የሚያመለክቱናቸው፡፡የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚላቸው ከግብፅ ምድር የወጡትን ትውልዶች ነው፡፡

ወገን ሁሉ

እዚህ ላይ “ወገን ሁሉ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው መላ አገሪቱን ነው፡፡የእሥራኤል ሕዝቦች ሁሉ የያዕቆብ ትውልዶች ናቸው፡፡የአሞፅ ትርጉም “አገሪቱ በአጠቃላይ”ወይም “ነገዱ በአጠቃላይ” (ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ከምድር ወገን ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄችኋለሁ

ይሄ ሊታዘዙለት ይገባቸው እንደነበረ የሚያመለክት ነው፡፡ይሄ ግልፅ በሆነ መልኩ ሊነገር ይችላል፡፡(በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትንና ግልፅ የሆነ መረጃ የሚለውን የሚለውን ይመልከቱ)

የምድር ነገዶች ሁሉ

እዚህ ላይ “ነገዶች”የሚለው ቃል አገራትንና ሕዝብን ይወክላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “በምድር ላይ ያሉ አገራት ሁሉ”ወይም “በምድር ላይ የሚገኙ ነገዶች ሁሉ”(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህ ስላደረጋችሁት ኃጢአት ሁሉ እበቀላችኋለሁ፡፡

የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንዳልተቀበሉ በግልፅ ማወቅ ይቻላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “ነገር ግን አልታዘዛችሁኝም፡፡ስለሆነም ስላደረጋችሁት ኃጢአት ሁሉ እቀጣችኋለሁ፡፡”( በግምት ላይ የተመሠረተ ዕውቀትና ግልፅ የሆነ መረጃ የሚለውን)

በእውነት እግዚአብሔር ሳይናገር ምንም ነገር አይፈፅምም፡፡…ነቢያት

ይሄ በአዎንታዊ መልኩ ሊገለፅ ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “በእውነትም እግዚአብሔር አምላክ ነገርን ወደ ግልፅ ያመጣዋል…ምንም ነገር ከማድረጉ በፊት ለነቢያት ይናገራል”ወይም “እግዚአብሔር ሰዎችን የሚቀጣው ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ዕቅዱን ካሳወቀ በኋላ ነው፡፡”( ሁለት አሉታዊ ነገሮች የሚለውን ይመልከቱ)

አንበሣ ሲያገሳ የማይፈራ ማን ነው?

አሞፅ አንበሣ በሚያጓራበት ወቅት ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ ሰዎችን በጥያቄ መልክ ያሳስባል፡፡ይሄ እንደ መግለጫ ሊወሰድ ይችላል፡፡የአሞፅ ትርጉም “አንበሣው አግስቷል፤ስለሆነም ሁሉም ሰው እንደሚፈራ እናውቃለን፡፡”ወይም “አንበሳ ስላገሳ በእርግጥም ሰው ሁሉ በፍርሃት ይዋጣል፡፡”(የተሳካ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)