am_tn/amo/01/11.md

3.2 KiB

ስለ ሶስትና ስለ አራት ኃጢአቶች

ይሄ ቅኔያዊ አነጋገር ነው፡፡ የተወሰነ ቁጥር ያላቸው ኃጢአቶች ተፈፅመዋል ማለት ሣይሆን ብዙ ኃጢአቶች የእግዚአብሔር ፍርድ እንዲመጣ ምክኒያት መሆናቸውን የሚያመለክት ነው፡፡ይሄ በአሞፅ 1፡3 ላይ እንዴት እንደሚተረጎም ይመልከቱ፡፡

ኤዶምያስ

እዚህ ላይ“ኤዶምስ”የሚለው ቃል የኤዶምያስን አገር ሕዝብ የሚያመለክት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የኤዶምያስ ሕዝብ ”( ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

መቅሰፍቴን ከማድረግ አልመለስም

እግዚአብሔር ቅጣትን ተግባራዊ የሚያደርግ እንደሆነ አፅንዖት ለመስጠት ሁለት አሉታዊ ነገሮችን ይጠቀማል፡፡ይሄ በአሞፅ 1፡3 ላይ እንዴት እንደሚተረጎም ይመልከቱ፡፡(በተዘዋዋሪ መንገድ ሃሣብን መግለፅ የሚለውን ይመልከቱ)

ወንድሙን አሳደደ

የኤዶምያስ ትውልድ ሲወርድ ሲዋርድ የመጣው የእሥራኤል ሕዝብ ዘር ከተመዘዘበት ከያዕቆብ ወንድም ከነበረው ከዔሳው እነው የሚል ግምት አለ፡፡እዚህ ላይ “ወንድሙ”የሚለው ቃል የሚወክለው የእሥራኤልን ሕዝብ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የእስራኤልን ሕዝብ አሳደደ” (ግምታዊ ዕውቀት፤ውስጣዊ ወይም ያልተገለፀ መረጃንና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ ይመልከቱ)

ርህራሄንም ሁሉ ጥሏልና

“ርህራሄን አላሳያቸውም”

ቁጣውም ሁልጊዜ ነድዷልና፤መዓቱንም ለዘላለም ጠብቋልና

እነዚህ ሁለት ሐረጎች ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሲሆን የቁጣውን መቀጠል አፅንዖት ለመስጠት ይደጋገማሉ፡፡“ንዴት” እና “ቁጣ” የተሰኙት አሕፅሮተ ሥም “የንዴት” እና “የቁጣን” ቅፅል በመጠቀም ሊተረጎሙ ይችላሉ፡የአሞፅ ትርጉም“ ማቋረጫ በሌለው መልኩ ይበሳጭና ዘወትር ይቆጣ ነበር”(ተመሳሳይነትንና አሕፅሮተ ሥምን ይመልከቱ)

ቁጣውም ሁልጊዜ ነድዷልና

ይሄ የማይቋረጥ ቁጣውን ለመግለፅ በማጋነን መልክ የቀረበ ነው፡፡(ሆን ብሎ አጋኖ መናገርንና አጠቃላይነትን ይመልከቱ)

ቴማንና ባሶራ

እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ስሞች እንዴት ሊተረጎሙ እንደሚገባ ተመልከቱ፡፡

የባሶራን አዳራሾች በእሣት ይበላል

እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ አዳራሾችን በእሣት ከሚበላ እሣት ጋር በማመሰሰል ይናገራል፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገርን ይመልከቱ)