am_tn/amo/01/05.md

2.1 KiB

ሃሣብን ማያያዝ

እግዚአብሔር በደማስቆ ላይ የፍርድ መልዕክቱን መናገር ይቀጥላል፡፡

ሰውዬውን አስወግድ

እዚህ ላይ “አስወግድ”ማለት ማጥፋት ወይም ማሳደድ ማለት ነው፡፡የልብስ ቁራጭ እንደሚቆረጥ ወይም አንድ ቅርንጫፍ ከዛፍ ላይ እንደሚቆረጥ ዓይነት ማለት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “ሰውዬውን ማጥፋት”ወይም “ሰውዬውን ማሳደድ”(-ምሣሌያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የአዌን ሸለቆ

ይሄ የአንድ ቦታ ሥም ሲሆን ትርጉሙም “የክፋት ሸለቆ”ማለት ነው፡፡ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት ነገሮች ደግሞ 1/ይሄ በዚያ ግዛት ሥር የሚገኝ የአንድ ሥፍራ ስም ነው፡፡ወይም 2/ይሄ የደማስቆ ወይም የአካባቢው ግዛት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የክፋት ሸለቆ”

በትር የያዘውንም

ይህ የዚያ ከተማ ወይም ግዛት ገዢ የሚለው ቃል ከዋናው ሃሣብ ጋር የሚገናኙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል ነውው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የ….. ገዢ”

የኤደን ቤት

ይሄ የአንድ ሥፍራ ስም ሲሆን ትርጉሙም “የደስታ ቤት” ማለት ነው፡፡ለዚህ ፍቺ ሊሆኑ የሚችሉት ነገሮች ደግሞ 1/ይሄ በዚያ ግዛት ሥር የሚገኝ የአንድ ሥፍራ ስም ነው፡፡ወይም 2/ይሄ የደማስቆ ወይም የአካባቢው ግዛት በሌላ ቃል ሲገለፅ ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም “የደስታ ቤት”(ስሞችና ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውሉ ቃላት እንዴት ነው መተርጎም የሚኖርባቸው? የሚለውን ይመለከቱ፡፡)

ቂር

ይሄ የሃራም ሕዝብ ከመጀመሪያ አንስቶ የነበሩበት የአንድ ግዛት ሥም ነው፡፡