am_tn/amo/01/03.md

2.6 KiB

ስለሶስት ወይም ስለ አራት ኃጢአቶች

ይሄ ቅኔያዊ አነጋገር ነው፡፡ይሄ የተወሰኑ ኃጢአቶች ብቻ ናቸው የተፈፀሙት ለማለት ሣይሆን ወደ እግዚአብሔር ፍርድ እንዲያመራ ያደረገው የብዙ ኃጢአቶች ድምር መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡

ደማስቆ

እዚህ ላይ “ደማስቆ”የሚወክለው በደማስቆ ከተማ ውስጥ ነዋሪ የሆኑትን ሰዎች ነው፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

መቅሰፍቴን ከማድረግ አልመለስም

እዚህ ላይ እግዚአብሔርደማስቆ በገለዓድ ላይ የፈፀመችው ነገር እህልን በብረት መንኮራኩር ወይም በመሣሪያ ከማበራየት ጋር ያመሳስለዋል፡፡(ነው፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ) ይመልከቱ)

ገለዓድ

እዚህ ላይ ገለዓድ የሚለው ቃል የገለዓድን ሕዝብ የሚያመለክት ነው፡፡የአሞፅ ትርጉም“ የገለዓድ ሕዝብ” (ነው፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የሚገናኙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ))

በአዛሄል ቤት ላይ እሣትን እልካለሁ

እዚህ ላይ እግዚአብሔር ከሚባላ እሣት ጋር በሚመሳሰልበት መልኩ በአዛሄል ቤት ላይ ፍርድን የሚያመጣ ስለመሆኑ ይናገራል፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገርን ይመልከቱ)

የአዛሄል ቤት

“ቤት”የሚለው ቃልበቤት ውስጥ ስለሚኖሩ ቤተሰቦች የተነገረ አባባል ነው፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የሚገናኙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ) በዚህ አውድ መሠረት ይሄ የሚያመለክተው ደማስቆ በነበረበት ሥፍራ ላይ በአገሪቱ ላይ ገዢ የነበሩትን ትውልዶች ነው፡፡(ከዋናው ሃሣብ ጋር የሚገናኙ ነገሮችን ለመግለፅ የሚውል ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

የወልደ አዴርን አዳራሾች ትበላለች

እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ ቅጥርን ከሚበላ እሣት ጋር ተመሳስሎ ነው የተነገረው፡፡(ምሣሌያዊ አነጋገሩን ይመልከቱ)

አዛሄል…ወልደ አዴር

እነዚህ የሰው ስሞች ናቸው፡፡