am_tn/act/25/11.md

1.4 KiB

የሐዋርያት ሥራ 25፡ 11-12

አያያዥ ዓረፍተ ነገር: ጰውሎስ ከፊስጦስ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡ እኔ ያደረኩት ነገር ለሞት የሚያበቃ ከሆነ "ለሞት ቅጣት የሚያበቃ ጥፋት ፈጽሜ ከሆነ" ክሳቸው ትክክል ካልሆነ "የከሰሱኝ ክስ ትክክል ካልሆነ" ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ልሰጠኝ አይችልም አማራጭ ትርጉሞች 1) ፊስጦስ ለእነዚህ በሐሰት ለከሰሱት ሰዎች አሳልፎ ልሰጠው የሚስችል ምን ሕጋዊ ሥልጣን የለውም ወይም 2) ጳውሎስ እያለ ያለው ያቀረቡት ክስ መሠረት ያሌለው ከሆነ ሀገረ ገዥው በአይሁዳዊያን ጥያቄ መሠረት ለእነርሱ አሳልፎ ልሰጠው አይገባም፡፡ ወደ ቄሣር ይግባኝ አለ "ቄሣር ይዳኘኝ ዘንድ በእርሱ ፊት መቅረብ እፈልጋለሁ" ፊስጦስ ከሸንጎዎቹ ጋር ተመካከረ በዚህ ሥፍራ ላይ “ሸንጎ” ተበሎ የተጠቀሰው በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ በአጠቃላይ የተጠቀሰው የአይሁድ ሸንጎ አይደለም፡፡ ይህ በሮም አገዛዝ ውስጥ ያለ ፖለቲካዊ ሸብጎ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "ፊስጦስ ከራሱ የአስተዳደር አማካሪዎች ጋር ተነጋገረ፡፡"