am_tn/act/25/01.md

1.7 KiB

የሐዋርያት ሥራ 25፡ 1-3

አጠቃላይ መረጃ: አሁን ፊስጦስ የቄሳሪያ አገረ ገዥ ሆኗል፡፡ አሁን ይህ በታኩ ውስጥ የተከናወነው ቀጣዩ ነገር ምን እንደሆነ ምልክት ሆኖ ያሳየናል፡፡ ፊስጦስ ወደ መንደሩ ገባ አማራጭ ትርጉሞች 1) በቀላሉ ፊስጦስ ወደ አከባቢው መጣ ወይም 2) ፊስጦስ አከባቢውን ማስተዳደር ጀመረ፡፡ (UDB). ከቄሣሪያ አንስቶ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ሄደ አማራጭ ትርጉሞች 1) ኢየሩሳሌም ወደ ላይ አድርጎ ማቀመጡ ኢየሩሳሌም ጠቃሚ መሆኗን የሚያሳይ ነው ወይም 2) ኢየሩሳሌም በተራራ ላይ ያለች ከተማ በመሆኗ ወደ ከፍታ መውጣቱን የሚያሳይ ነው፡፡ ጳውሎስ ላይ ክስ አቀረቡበት ይህ በፍርድቤት መደበኛ ክስ ማቅረባቸውን ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "ጳውሎስ ሕግጋትን መተላለፉን የሚያሳይ ክስ አቀረቡበት፡፡" በፊስጦስ ፊት አጥብቀው ከሰሱት "ፊስጦስን ለመኑት" ወይም "ፊስጦስን ጠየቁት" ይጠራው ዘንድ . . . እነርሱም እርሱን መግደል ይችሉ ዘንድ "ፊስጦስ ጳውሎስን ይጠራው ዘንድ . . . አይሁዳዊያንም ጳውሎስን መግደል ይችሉ ዘንድ" ይጠራው ዘንድ "ይልከው ዘንድ" በመንገድ ላይም እነርሱ መግደል ይችሉ ዘንድ ጳውሎስን በመንገድ ላይ ተደብቀው ልገድሉት ይፈልጉ ነበር፡፡